የኢፌዲሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጥሪ በተደረገላቸው ዲያስፖራዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው ለት ሰጥቷል።

▪️ወደ ሀገር ቤት ለሚመጡ ዲያስፖራዎችን አስመልክቶ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ግቢ ውስጥ ዛሬ ረፋድ አካባቢ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።

▪️ ለሀገሬ ህልውና በአንድ ልቦና በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ዝግጅት ህብረብሔራዊ ወንድማማችነትን ለትውልደ ኢትዮጽያውያኑ ሚያሳዩ ፣ ስፖርታዊ ውድድሮች ፣ እና ጨዋታዎች እንዲሁም ባህላዊ ሙዚቃ concert  እንደሚኖሩ ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ተናግረዋል። አያይዘውም እንግዶችን መቀበል እና ፌስቲቫሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የሁሉም ሀላፊነት ነው ብለዋል።በመንግስት በኩል የፀጥታ ችግር የሌለባቸው ቦታዎች ላይ ዝግጅቶቹ እንደሚካሄዱ ገልፀጿል። በመዲናችን በአዲስአበባም አፍሪካ አዳራሽ ፣ስታዲየም አካባቢ ዝግጅቶቹ ሊካሄዱ እንደሚችሉ ገልፀዋል። በክልል ከተምችም ከክልሎች  ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን በጋራ እየሰሩ እንደሆነ እና በተመረጡ ከተሞች ላይም መርሀ-ግብሩ እንደሚከናወን ገልፀዋል። የግል ሴክተሩም የኪነጥበብ ወይም ስፖርታዊ አካላት እንደሚሆኑ እና ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሲገልፆ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት የታሰበ ነገር ሳይሆን እንደ ተቋም ዲያስፖራው ባህሉን በደንብ እንዲያውቅ እና ትውፊቶቹን እንዲገነዘብ ብሎም በኪነ-ጥበቡ  በመሸመት ለኛ ገፆታ ግንባታ ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚ ፋይዳ ይዞ ሚመጣ ነገር ነው ብለዋል።

▪️ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ በበኩላቸው ባህል እና ስፖርት የሀገር አቀፍ አብይ ኮሚቴ አንድ አባል ነው።ስለዚህም ነው እንደ ተቋም ሀገራችን በ 1 እጇ ጦርነቱን እያሸነፈች መሆኑን በሌላ መልኩ ደግሞ ባህሏንም ፣ ትውፊቷንም እያሳየች ነው ሚለውን ለአለም ለማሳየት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል። ኢትዮጵያ በእንግዳ ተቀባይነቷ ምትታወቅ ሀገር ናት እንግዳ ሲመጣ እንኳን ደና መጣችሁ በማለት የቡና ስነ-ስርዓት በየቦታው እንዲኖር እና ሆቴሎችም እንግዳ ማረፊያዎችም ከዚ ጋር ተያይዞ ቅናሽ እንዲያደርጉላቸው እየሰራን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል።
የተለያዩ ስፖርታዊ ጉዳዮች እንደሚካሄዱ ገልፀዋል ከዚህም መሀከል መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ፣ የፈረስ ጉግስ ትርኢት እንዲሁም የገና በአል እየደረሰ እንደመሆኑ መጠን የገና ጨዋታዎች እንደሚካሄዱ ገልፀዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.