ፌራን ቶሬስ ባርሴሎናን ተቀላቅሏል።
▪️ፌራን ቶሬስ ከ ማንቸስተር ሲቲ ባርሴሎናን መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል። ይህ የ21 አመት ስፔናዊ ተጫዋች በ 2020 ነበር ቫሌንሽያን ለቆ ማንቸስተር ሲቲን በ 20.8 ሚሊዮን ፓውንድ የተቀላቀለው።
▪️በማንቸስተር ሲቲ ቤት በአጠቃላይ 40 ጨዋታዎችን ማድረግ ሲችል 15 ጎል ሲያስቆጥር 4 ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
▪️ፔፕ ጋርዲዮላ ልጁ ጥሩ ብቃት ያለው ተጫዋች ነው ግን እዚ ደስተኛ ካልሆነ እንዲቆይ አልፈልግም ብሏል።
▪️ብሉግራናዎቹ ለፌራን ቶሬስ 55 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍለዋል 5 አመት ካምፕ ኑ ሚያቆየውን ውል ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል። ትላንት ወደ ባርሴሎና ከ ከወኪሎቹ ጋር በመሆን የበረረው ፌራን ቶሬስ ዛሬ የሜዲካል ምርመራውን ያደርጋል እንዲሁም በይፋ የባርሴሎና ተጫዋች መሆኑ ይታወቃል ተብሏል።
ሚካኤል ደጀኔ።