የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ስለ አፍሪካ ዋንጫ ሚሉትአለ።
▪️የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፀሀፊ አቶ ባህሩ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አቶ ውበቱ አባተ ወቅታዊ በሆነና በብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅት ዙሪያ በኢሌሌ ሆቴል ዛሬ 8:00 መግለጫ ሰጥተዋል።
▪️ አሰልጣኝ አቶ ውበቱ አባተ ከፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች እንዲሁም ምክትል አሰልጣኞች ጋር ውይይት እንዲሁም ምክክር በማድረግ ግብአት መውሰዳቸውን እንዲሁም ከተመረጡት ተጫዋቾች ጋር ያደረግነውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቪድዮ በማየት ያደረጉትን እንቅስቃሴ ገምግመናል ክፍተት ያየንበት ቦታ ለመስራት ሞክረናል ባለን አጭር ጊዜ ብለዋል። በኪሎ የጨመሩ እና የቀነሱ
▪️ ከሚዲያ አካላት ለቀረበላቸው ጥያቄም መልስ እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል። የተጫዋቾች ምልመላ ላይ ዴቪድ በሻህ የመለመላቸው እና በውጭ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ለምሳሌ እንደ ዳንኤል ንጉሱ የተባለ የ ኖርዌይ ሊግ ሚጫወት በረኛ ለምን አልተካተተም የሚል ነው። ሀይላይቱን ገብቼ አይቼዋለሁ ግን ያን ያህል የተጋነነ ብቃት የለውም። በዛ ላይ 12 ቀን እየቀረን እነሱንቡድኑ ውስጥ Inject ማድረግ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ብዬ ስላመንኩበት ነው ብለዋል።
▪️አቶ ባህሩ በበኩላቸው ጉዞውን እንዲሁምቆይታቸውን አስመልክቶ 51 ሚሊዮን ብር ከመንግስት የጠየቁ ቢሆንም የተሰጣቸው ግን 31 ሚሊዮን ብር እንደሆነ እና መንግስት አሁን ካለበት ጫና እና ወቅታዊ ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይሁን ብለናል እናመሰግናለን ብለዋል። አክለውም ብሄራዊ ቡድኑ የፊፋ ኤጀንት አለው ከ ካምፒንግ አንስቶ እስከ ጃንዋሪ 5 ድረስ ኤጀንታችን በሚያመቻቸው መሠረት በትንሹ 2 የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያካሄዱ እንደ አሰልጣኙ ፈቃድ 3 ም ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።ሀገሮቹ ሞሮኮ ፣ ሱዳን ፣ ዚምባቡዌ እንደሆኑ ነው የተገለፀው። በተጨማሪም ብሄራዊ ቡድኑ የፊታችን ቅዳሜ የሽኝት ፕሮግራም እንዲሁም የባንዲራ ርክክብ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።
ሚካኤል ደጀኔ።