ዛሬ የተሰሙ አጓጊ የዝውውር ጭምጭምታዎች።

▪️ዋትፈርድ ኮላሲናችን  ለማስፈረም ተዘጋጅቷል። የ28 አመቱ የአርሰናል ተከላካይ ሲድ ኮላሲናች ባሳለፍነው አመት በውሰት ወደ ጀርመኑ በማቅናት በሻልክ 04 ማሳለፉ ይታወሳል። ዘንድሮም ብዙ እድል እየተሰጠው ያልሆነው ይህ bosniaዊ በአዲሱ የዋትፈርድ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ጥሪ ከቀረበለት አይኑን እንደማያሽ The telegraph ዘግቧል።

▪️ቦርሺያ ዶርትሙንድ የጁድ ቢሊንጋም ወንድም ለማስፈረም መዘጋጀቱን Football insider ዘግቧል። ይህን የሚያደርጉት ጁድ ቢሊንጋም በsignal iduna park እንዲቆይላቸው ለማድረግ በማሰብ ነው ተብሏል። ከልጁ ወኪል ጋር ውሉን እንዲያራዝም እየተነጋገሩ ይገኛሉ። ጁድ ቢሊንጋም ገና በ 18 አመቱ ጥሩ እና ድንቅ ብቃቱን በዶርትሙንድ እያሳየ ሚገኝ ታዳጊ ተጫዋች ነው። በዶርትሙንድ ቤትም እስከ 2025 ሚያቆየው ኮንትራት እንዳለ ይታወቃል።

▪️አንቶኒ ማርሻል ማንቸስተር ዩናይትድ በጥር የዝውውር መስኮት መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ከተባለ ምርጫው ሲቭያን መቀላቀል እንደሆነ አስታውቋል። ባርሴሎና እና ጁቬንትስ የዚህ ልጅ ፈላጊዎች ናቸው። አንቶኒ ማርሺያል በ2015 ሞናኮን ለቆ ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለ ሲሆን ውሉን በ2019 ካደሰ በኋላ 3 አመት ዩናይትድ ቤት ይቀረዋል። እሱን በጥብቅ ከሚፈልጉት 3 ክለቦች አንቶኒ ማርሻል ብዙ የመጫወት ዕድል ወደ ሚያገኝበት ሲቭያን ምርጫው እንደሚያደርግ ነው የተገለፀው። ወኪሉ philip lenboye ለ sky sport እንደተናገሩት ከሆነ አንቶኒበዩናይትድ ቤትየመጫወት እድል እያገኘ ስላልሆነ በጥር ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል ብሎ ሀሳቡን ገልጿል። ማርሻልዘንድሮ ለ ቀያዮቹ5 ጊዜ ብቻ የተሰለፈሲሆን ሁሉንም ተቀይሮ ነው መግባት የቻለው።

▪️ሚኬል አርቴታ ንኬቲያን የእቅዱ አንድ አካል እንደሆነ ገልጿል።
የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ክለቡ የኤዲ ንኬቲያን ውል እንዲያድስ እንደሚፈልግ ትላንት  ሰንደርላንድ ላይ ድንቅ ብቃቱን ካሳየ እና  ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ተናግሯል። እሱን በEmirates ለማቆየት እየሰራን ነው። ምንም ሚካበድ ነገር የለውም ልጁ ብቃት አለው መጫወት ነውሚፈልገው ሜዳ ላይ ጊዜ እንድትሰጠው ነው ሚፈልገው። እኔም ይህን ነገር ከግምት ውስጥ የምከት ይሆናል ብለዋል ስፔናዊው የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.