ተጠባቂዎቹ የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች።
▪️ የቦክሲንግ ዴይ ስም አመጣጥ መለስ ብለን ስናይ ድሮ በእንግሊዝ ሀገር ሀብታሞች ለድሀው ማህበረሰብ ስጦታ ሚያበረክቱለት ቀን ነው። ከሀይማኖት ጋርም በተያያዘ ሲሆን st.Stephen’s እያሉ ቀኑን በ አየርላንድ ውስጥ ሲያከብሩት በስፔን ሀገር ያሉ ካታሎናውያኑ በስፔን ውስጥ እንዲሁ ሚያከብሩት በአል ነው።
▪️በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ማለትም በ ሀንጋሪ ፣ ጀርመን ፣ ፖላንድ ፣ እና ኔዘርላንድ በቦክሲንግ ዴይን እንደ 2ኛ የገና በአላቸው ያከብሩታል። ይህም ቀን Dec 26 ማለትም የፊታችን እሁድ ነው። ቦክሲንግ ዴይ ለመጀመሪያ ጊዜ መካሄድ የጀመረው በ1957 ሲሆን ከዛን ጊዜ ወዲህ ባህላዊ ወጉን ሳይለቅ ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር እዚ ደርሷል።
▪️የዘንድሮ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች የፊታችን እሁድ ቀጥለው ሲውሉ።
ሊቨርፑል ከ ሊድስ 9:30
ዎልቭስ ከ ዋትፈርድ 9:30
በርንሌይ ከ ኤቨርተን 12:00
ማንቸስተር ሲቲ ከ ሌስተር ሲቲ 12:00
ኖርዊች ሲቲ ከ አርሰናል 12:00
ቶተንሀም ከ ክሪስታል ፓላስ 12:00
ዌስትሀም ከ ሳውዝሀምፕተን 12:00
አስቶንቪላ ከቼልሲ 2:30
ብራይተን ከ ብሬንትፈርድ 5:00
ሰኞ
▪️ሁለትጨዋታዎችን በኮቪድ ምክንያት ሳያደርግ የቆየው ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ሴንት ጄምስ ፓርክ አቅንቶ ውጤት ቀውስ ውስጥ ሚገኘው ኒውካስል ዩናይትድን ምሽት 5:00 ይካሄዳል።
ሚካኤል ደጀኔ