የቤት ኪንግ ኢትዩጵያ ፕሪሚየር ሊግ አጓጊነቱ አሁንም ቀጥሏል።
▪️8ኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረቡዕ ጀምረው ቀጥለዋል። መከላከያ ከሲዳማ ቡና ያለ ግብ አቻ ሲለያዩ መሪውን ከቅርብ ተከታዩ ጋር ያገናኘው የፋሲል ከነማ እና የባህርዳር ከተማ ጨዋታ ምንም ጎል ሳይታይበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
▪️ሀሙስ ሀድያ ሆሳዕና ሁለት ጊዜ ከመመራት ተነስቶ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ድሬዳዋ ከተማን 3-2 አሸንፏል። ሀድያ ሆሳዕና ባሳለፍነው ሳምንት መከላከያን ካሸነፉ በኋላ ያሳኩት ተከታታይ ድል ነው። አዲስአበባ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር 1 አቻ ተለያይተዋል።
▪️በምክትል አሰልጣኝ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታ ሚመራው ቅ/ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን 1-0 ሲያሸንፍ ጎሏን የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ በስሙ አስመዝግቧል።
▪️ኢትዮጽያ ቡና ቤት በተጫዋችነት አብረው ጊዜ ያሳለፉትን በአሰልጣኝነት ደግሞ የተለያየ ቡድን ይዘው የተገናኙት ጳውሎስ ጌታቸው እና ካሳዬ አራጌ በ8 ኛው ሳምንት ቸፈተገናኝተው የካሳዬው ኢትዮጵያ ቡና 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል። ጎሏንም ዊልያም ሰለሞን አስቆጥሯል። እዚ ጨዋታ ላይ “ጌታነህ ጀግናችን ማልያህን እፈልጋለሁ ፣ ማልያህን ስጠኝ ላለች የወልቂጤ ከተማ ደጋፊ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ማልያውን ጌታነህ አውልቆ ተሰጥቷታል።
▪️አርባምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ 1 አቻ ሲለያዩ ጅማአባጅፋር በሰበታ ከተማ 1-0 ተሸንፏል።
የደረጃ ረንጠረዡን
▪️ፋሲል በ15 ነጥብ ሲመራ
ባህርዳር ከተማ ፣ ቅ/ጊዮርጊስ ፣ኢትዮጵያ ቡና በእኩል 14 ነጥብ ከ 2-4 ያለውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።
▪️ወራጅ ቀጠናው ድሬዳዋ በ 8 ነጥብ ሰበታ በ 7 ነጥብ እንዲሁም ጅማ አባጅፋር በ1 ነጥብ የደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛል።
▪️የ9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም ሲቀጥሉ።
ፋሲል ከተማ ከ መከላከያ ቀቀ 9:ዐዐ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከ አዲስአበባ ከተማ በ12:00 በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።
ሚካኤል ደጀኔ።