ታላቁ የኤልክላሲኮ ጨዋታ።

183ኛው የኤልክላሲኮ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።ሎስ ብላንኮቹ ወደ ካምፕ ኑ አቅንተው ባርሴሎናን ጎብኘት ባደረጉበት ጨዋታ በክረምቱ ባየርሙኒክን ለቆ ሪያል ማድሪድን በተቀላቀለው እንዲሁም የመጀመሪያ የኤል ክላሲኮ ጨዋታውን ያካሄደው ዴቪድ አላባ ከእረፍት በፊት ባስቆጠራት ግብ 1-0 እየመሩ ለእረፍት ወተዋል።ከእረፋት መልስ የጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የተገኘውን መልሶ ማጥቃት ሉካስ ቫስኬዝ በአግባቡ በመጠቀም መሪነቱን ወደ 2 ያሰፋ ጎል ማስቆጠር ችሏል።ከ አራት ደቂቃ በኋላም የዳኛው ፊሽካ በሚጠበቅበት ሰአት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከማንቸስተር ሲቲ  ወደ ባርሴሎና ያመራው እና የመጀመሪያ የኤል ክላሲኮ ጨዋታውን ተቀይሮ ገብቶ ማድረግ የቻለው ሰርጂኦ ኩን አጉዌሮ ቡድኑ ከባዶ መሸነፍ የታደገች ኳስ ከመረብ አዋህዷል።
▪️እ.ኤ.አ  ከ 2004 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊዮኔል ሜሲንም ሰርጂዮ ራሞስንም ሳያካት የተካሄደው ኤል ክላሲኮ ቀዝቀዝ ያለ ጨዋታ የታየበት ነበር።ከዚህ ጨዋታ በፊት 182 ጊዜ የተገናኙት እነዚህ ሁለት ቡድኖች 75ጊዜ ማድሪድ የበላይነቱን ሲወስድ ዛሬ 76ኛው ሆኖ ተመዝግቧል።በሁሉም ጨዋታዎች ባርሴሎናን በተከታታይ 4 ጊዜም ማሸነፍ ችለዋል ከ1965 ወዲህ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
▪️የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሮናልድ ኪውማን በታሪክ 3 ተከታታይ የኤልክላሲኮ ጨዋታዎች የተሸነፈ 2ኛው አሰልጣኝ ሆኗል።የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ በሰጡት አስተያየት ከትልቅ ቡድን ጋር ነው የተጫወትነው ኳስ ተጋጣሚዎቻችን ጋር ሲሆን ያሳየነው የመከላከል መንፈስ በጣም አስደስቶኛል። በውጤቱም ረክቻለሁ ሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

ሚካኤል ደጀኔ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.