ቀዩ እሁድ።

▪️ግዙፉ ኦልትራፎርድን መዳረሻው ያደረገውና እነዚህ 2 በታሪክ ባለአንጣ የሆኑ ክለቦችን ያገናኘው የ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባልተጠበቀ መልኩ በእንግዳው ሊቨርፑል 5-0 በሆነ አሸናፊነት ተጠናቋል።
▪️ኦሌ ጎነር ሶልሼር ፖል ፖግባ እና ጄደን ሳንቾን ወደ ተቀያሪ ወንበር አውርደው ጨዋታውን ሲጀምሩ የርገን ክሎፕም በአንፃሩ ሳዲዮ ማኔ እና ጆኤል ማቲፕን ወደ ተቀያሪ ወንበር አውርዶ ጨዋታውን ጀምሯል።
▪️ከእረፍት በፊት 4 ጎሎችን ያስተናገደው ባለሜዳው ቡድን ማን.ዩናይትድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜም ሆኗል።
▪️በጨዋታው 3ጎሎችን ማስቆጠር የቻለው ሞሀመድ ሳላህ በፕሪሚየር ሊጉ ብዙ ጎል ያስቆጠረ አፍሪካዊ ተጫዋች መሆን ችሏል።106 ጎሎችን በማስቆጠር በቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች ዲዲዬ ድሮግባ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በእጁ አስገብቷል።ይህ ግብፃዊ ሌላም ሪከርድ አስመዝግቧል እ.ኤ.አ በ2003 April ወር ላይ የሪያል ማድሪዱ ቸጫዋች ሮናልዶ ናዛ️ሪዮ ዴሊማ ኦልድትራፎርድ ላይ ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ማንም ተጫዋች ኦልድትራፎርድ ሜዳ ላይ 3ጎል አስቆጥሮ አያውቅም።ሞ ሳላህ ይህን ታሪክም በምሽቱ ጨዋታ መፃፍ ችሏል።
▪️በምሽቱ ጨዋታ 5ጎሎችን የተከናነቡት የኦሌ ጎነር ሶልሼር ልጆች በሜዳቸው በሚያደርጉት ጨዋታ 5ጎል እና ከዛ በላይ ተቆጥሮባቸው ሲሸነፉ ይህ ከ 1955 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
▪️ከዕረፍት መልስ ሜሰን ግሪንውድን ቀይሮ የገባው ፖል ፖግባ ሜዳላይ መቆየት የቻለው 15 ደቂቃ ብቻ ነው።ናቢ ኪዬታ ላይ በሰራው ከባድ ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
▪️ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ በቀጣይ ሳምንት ቶተንሀምን ከሜዳው ውጪ ከዚያም በደርቢው ማንቸስተር ሲቲን በሜዳው ሚያስተናግድ ይሆናል።ኦሌ ጎነር ሶልሼር ላይ ጣታቸውን ሚቀስሩ ደጋፊዎችም ከቀን ወደ ቀን በርከት እያሉ ነው።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.