በቫሌንሺያ የተካሄደው ግማሽ ማራቶን ።

▪️የ23 አመቷ ለተሰንበት ግደይ የ 10,000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት መሆኗ ይታወሳል።ዛሬም ቫሌንሽያ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን በኬንያዊቷ ሩት ቼፕጌቲች ተይዞ የነበረውን 1:04:52 ሪከርድ ከ 1:50 ሰከንድ ጭምር በማሻሻል በ1:02:52 ሰከንድ 1ኛ ሆና ጨርሳለች።

▪️በግማሽ ማራቶኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የሮጠችው የተሰንበት ግደይ ቫሌንሽያ የ5,000 ሜትር የአለም ሪከርድን ወደ 14:06:02 ያሻሻለችበት መድረክም እንደሆነ እናስታውሳለን ።

▪️በሴቶቹ ኢትዮጽያዊያን ደምቀው በታዩበት የግማሽ ማራቶን ገነቱ ሞላልኝ እና በውድድሩ ተጠብቃ የነበረው ያለምዘርፍ የኋላው በእኩል ሰከንድ ግን በማይክሮ ሰከንድ ተለያይተው 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ተከታትለው ገብተዋል።

▪️በወንዶቹ  ኬንያውያን ውድድሩን ተቆጣጥረው ከ 1 እስከ 5ኛ ደረስ ይዘው ውድድሩን ሲያጠናቅቁ 1ኛ የወጣው alex kipchumba (58:07) ሲገባ kipruto 2 ሰከንድ ብቻ ዘግይቶ (58:09) ተከትሎ ገብቷል daniel mateiko (58:09) 3ኛ ሆኖ የጨረሰበት ሰአት ነው።ኢትዮጵያዊው ሙክታር እንድሪስ 58:40 6ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.