9ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ተከናውነዋል።
▪️ቀን 8:30 የጀመረው እና ስታም ፎርድ ብሪጅ መዳረሻው ያደረገው የቼልሲ እና የኖርዊች ጨዋታ ቼልሲ 7-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። የቶማስ ቱኸሉ ቡድን ዘንድሮ ክለባቸውን የተቀላቀለው ግዙፉ ቤልጂየማዊ ሮሜሉ ሉካኩ እና አጣማሪውን ቲሞ ወርነርን ሳይዙ ወደሜዳ ቢገቡም ኖርዊች ላይ ምንም አይነት ርህራሄ ሳያሳዩ 7 ጎሎች አስቆጥረዋል።ሜሰን ማውንት ሀትሪክ ሲሰራ ሪስ ጄምስ፣ሀድሰን ኦዶይ፣ቺልዌል እንዲሁም የኖርዊቹ ተከላካይ ማክስ አሮንስ ራሱ ላይ አንዷን ግብ አስቆጥሯል።ቼልሲ የዘንድሮው ውድድር ከጀመረ 16 የተለያዩ ተጫዋቾች ጎል አስቆጥረዋል።ሜሰን ማውንት 17ኛው ተጫዋች ሆኗል።የቼልሲ ቡድን ስብስብ ብዛትም ጥራትም ያለው መሆኑን ያሳያል።
▪️11 ሰአት ላይ 4 ጨዋታዎች ሲካሄዱ የፓትሪክ ቪዬራው ክሪስታል ፓላስ ስቲቭ ብሩስን ያሰናበተው ኒውካስትልን በ ሴልኸርስት ፓርክ አስተናግዶ 1አቻ በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።
▪️በክላውዲዮ ራኔሪ ሚመራው ዋትፈርድ ወደ ጉዲሰን ፓርክ አቅንቶ የራፋ ቤኒቴዙን ኤቨርተንን 5-2 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈው ተመልሰዋል። ኤቨርተኖች ጨዋታውን 2 ጊዜ የመምራት እድል ቢያገኙም ውጤቱን አስጠብቀው መቀጠል ሳይችሉ ቀርተዋል። ቶም ዴቪስ ጨዋታው በተጀመረ በ130 ሰከንድ ያስቆጠራት ግብ ኤቨርተን በሜዳው ሲጫወት የገባች ፈጣኗ ግብ ሆና በታሪክ ተመዝግባለች።የጨዋታ ኮከብ የተባለው ጆሺዋ ኪንግ ከ29 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የጎል ድርቅ በኋላ የቀድሞ ክለቡ ኤቨርተን ላይ 3ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል።
▪️ሊድስ ዎልቭስን አስተናግዶ 1 አቻ ሲለያዩ ለዎልቭስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የኦስትሪያውን ሳልዝበርግ ለቆ ዎልቭስን የተቀላቀለው ሁዋንግ በ 10ደቂቃ ሲያስቆጥር በፕሪሚየር ሊጉ 4ኛ ጎሉ ሆና ተመዝግባለች። ለሊድስ ዩናይትድ የአቻነቷን ግብ ሮድሪጎ የጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
▪️ሳውዝሀምፕተን በርንሌይን በሜዳው ሴንት ሜሪ ጋብዞ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል። ጎሎቹን ሊቭራሜንቶ እና ብሮሀ ለሳውዝሀምፕተን ሲያስቆጥሩ ለብራይተን 2ቱንም ግቦች ዘንድሮ ሊዮንን ለቆ በርንሌይን የተቀላቀለው ማክስዌል ኮርኔ በስሙ አስገኝቷል።
▪️የግራም ፖተሩ እና 4ኛ ደረጃን ይዞ የተቀመጠው ብራይተን ሆቭ አልቢዮን ከማንቸስተር ሲቲን በሜዳው አሜክስ ምሽት 1:30 ሲል አስተናግዶ 4-1 በሆነ ውጤት ሽንፈትን ቀምሰዋል። የፔፕ ጋርዲዎላ ልጆች እንደተለመደው ኳስ በመያዝ እና የተጋጣሚን ተከላካይ ክፍል ሰብሮ ጎል ለማግባት 13 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀባቸው በጀርመናዊው ኢካይ ጉንዶጋን አማካኝነት የመጀመሪያ ጎል ያስቆጠሩ ሲሆን በ28 እና በ31ኛው ደቂቃ ታዳጊው ፊል ፎደን አከታትሎ ባስቆጠራቸው 2ግቦች ሲቲ 3-0 እየመራ ለእረፍት ወተዋል።ከእረፍት መልስም የጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ በሪያድ ማህሬዝ አማካኝነት 1ግብ አክለዋል ለብራይተን ከባዶ መሸነፍ ያዳነቻቸውን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አሌክሲስ ማካሊስተር በ 81 ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።
ሚካኤል ደጀኔ።