የዘንድሮ የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ተጀመረ።

▪️የ 2014 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ጥቅምት 7  የጀመረ ሲሆን የመከሰፈቻ ጨዋታውም በ ሀዋሳ ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር መሀከል ቀን 8:00 የተደረገ ሲሆን ባለሜዳው ሀዋሳ ከነማ በ መስፍን ታደሰ ብቸኛ ጎል 1-0 ማሸነፍ ችሏል።

▪️12:00 ላይ ድሬዳዋ ከነማ ከወላይታ ዲቻ የተገናኙ ሲሆነሰ መደበኛው 90ደቂቃ ሊጠናቀቅ 2 ደቂቃ ሲቀረው የድሬዳዋ ከነማው ሄኖክ አየለ ባስቆጠራት ግብ 1-0 አሸንፈው ወተዋል።

▪️ሰኞም 2 ጨዋታዎች ቀጥለው ተካሂደዋል 9:00 ሲል በተካሄደው የአዳማ ከነማ እና የወልቂጤ ከነማ ጨዋታ 1 አቻ በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ አርባምንጭ ከተማ ከ መከላከያ 12:00 ሲል ያደረጉት ጨዋታ 58 ደቂቃ ላይ የመከላከያው አጥቂ ኦኩቱ ኢማኑኤል ባስቆጠራት ግብ መከላከያ ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ ከሜዳ ወጥቷል።

▪️ማክሰኞ ጥቅምት 9 ባህርዳር ከነማ ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገውን አዲስአበባ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ቀን 9:00 ሲል አካሂደው ነበር። ባህርዳር ከነማ በተመስገን ደረሰ፣ኦሴ ማውሊ ግብ ታግዞ 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

▪ይህ ጨዋታ ከመጠናቀቁ በኋላ የጀመረው የኢትዮጵያ ቡና እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ያለምንም ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

▪️የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ የተካሄዱ ሲሆን የአምናው ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ገን ቀን 9:00 ላይ የተጫወቱ ሲሆን ፋሲል ከነማ 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል 3ቱንም የፋሲል ጎሎች ፍቃዱ አለሙ በስሙ ሲያስቆጥር የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ሀትሪክ ሰሪ ሆኖ ስሙ ተመዝግቧል ለ ሀድያ ሆሳዕና ከባዶ መሸነፍ ያላዳነችውን ግብ ባዬ በ45 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። ይህ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት አዲሱን ዋንጫ የተበረከተላቸው አፄዎቹ በ አምበላቸው ያሬድ ባዬ አማካኝነት ከፍ አድርገው አንስተዋል።

▪️12:00 ሲል ሰበታ ከነማ ከ ቅ/ጊዮርጊስ የመጠረሻውን መርሀ ግብር ያከናወኑ ሲሆን ያለ ምንም ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን ጨርሰዋል።

 

 

ሚካኤል ደጀኔ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.