ሊቨርፑል በድል ጎዳና።
▪️ሊቨርፑል ወደ ቪካሬጅ ሮድ አቅንቶ ዋትፈርድን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
▪️የየርገን ክሎፑ ሊቨርፑል ያለ ቋሚ በረኛው አሊሰን ቤከር እና ያለ መሀል ሜዳ ተጫዋቹ ፋቢንሆ ጨዋታውን ያደረገ ሲሆን ይፈተናል ተብሎ ሲጠበቅ በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።
▪️ጨዋታው ከተጀመረ በ9ኛው ደቂቃ ላይ ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ቡድኑን ቀዳሚ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል።ከ 28ደቂቃ በኋላም ለሊቨርፑል በብዙ ጨዋታዎች ከቋሚነት አሰላለፍ ውጪ እየሆነ የነበረው እና የዲዬጎ ጆታን ቦታ ተክቶ የገባው ሮቤርቶ ፊርሚኖ ለቡድኑ 2ኛ የሆነች ግብን አስቆጥሮ ቡድኖቹ ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
▪️ከእረፍት መልስም ተጋጣሚውን ተጭኖ እና በተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርግ ያመሸው የክሎፑ ሊቨርፑል በ52 ደቂቃ ብራዚሊያዊው ፊርሚኖ ለሱ 2ኛ ለቡድኑ ደሞ 3ኛ የሆነች ግብ ከመረብ አሳርፏል።ከ 2 ደቂቃ በኋላም በጨዋታው ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ የነበረው ግብፃዊው ሞሀመድ ሳላህ ለቡድኑ 4ኛ ግብ አስቆጥሯል።በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ሮቤርቶ ፊርሚኖ ለቡድኑ 5ኛ ግብን ማስቆጠር ሲችል ለሱ ደሞ 3ኛው ሲሆን ሀትሪክ መስራት ችሏል።
▪️አዲሱ የዋትፈርድ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሽንፈት የጀመሩ ሲሆን በጨዋታው 1 ጎል ማስቆጠር የቻለው ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎል ብዛት 100 አድርሷል። ይህም ከዲዲዬ ድሮግባ ፣ ከቡድን አጋሩ መሀመድ ሳላህ ቀጥሎ 3ኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ያደርገዋል።
▪️ነገ ሊቨርፑልን ከተረከቡ 6 አመት ሚሞላቸው የርገን ክሎፕ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት በውጤቱ ደስተኛ መሆናቸውን እና በአሁን ሰአት ከ ሞሳላህ የተሻለ ተጫዋች የለም ሲሉ ግብፃዊውን አሞካሽተዋል።
ሚካኤል ደጀኔ