በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን።
▪️ለ2022ቱ የኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ውድድሮች እየተካሄዱ አንዳለ ይታወሳል።
▪️ምድብ 7 ላይ የተመደበው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንተው በ FNB ስታዲየም ከ ደብቡ አፍሪካ አቻው ጋር ጨዋታውን አካሂዶ ነበር።
▪️እስከ 2,000 የሚሆኑ ደጋፊዎች በ ስቴዲየም የተገኙ ሲሆን የመጀመሪያው አጋማሽ ጌታነህ ከበደ ራሱ ላይ ባስቆጠረው ጎል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 1-0 እየተመራ ለ እረፍት ወተዋል።
▪️ከእረፍት መልስም ተጨማሪ ጎል ሳይታይበት ጨዋታው ተጠናቋል።
▪️የፈጠሩትን ጥቂት እድል በአግባቡ አለመጠቀማቸው እና መሀል ሜዳው ላይ የተወሰደባቸው ብልጫ ዋልያዎቹ ከጨዋታው ምንም ነገር ሳይዙ እንዲወጡ ያረገ ምክንያት ነው።
▪️በዚህም መሠረት ደቡብ አፍሪካ 10 ነጠብ በመያዝ የምድቡ አናት ላይ ስትገኝ ጋና በ 9 ነጥብ ሁለተኛ ኢትዮጵያ በ 3 ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ዚምባቡዌ በ 1 ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች።
ሚካኤል ደጀኔ