ተጠባቂው የከባድ ሚዛን ፍልሚያ ተከናወነ።
▪️ከትላንት በስቲያ በላስ ቬጋስ ቲ-ሞባይል አሪና በተካሄደው የከባድ ሚዛን ፍልሚያ የቀበቶው ባለቤት ኢንግሊዛዊው ታይሰን ፊውሪ እና ተጋጣሚው አሜሪካዊው ዲኦንቴይ ዋይልደር ነበሩ።
▪እስከ 11 ዙር የሄደው የነዚህ 2 ቡጢኞች ፍልሚያ ጥሩ ፉክክር የታየበት ሲሆን ኢንግሊዛዊው ዘ ጂፕሲ ኪንግ እየተባለ ሚጠራው ታይሰን ፊውሪ ዲዮንቴይ ዋይልደር 11ኛ ዙር ላይ በመዘረር አሸንፎታል።
▪️ለ 3ተኛ ጊዜ የተገናኙት እነዚህ ተፋላሚዎች እ.ኤ.አ 2018 December ወር ላይ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት ጨዋታውም በዳኞች ውሳኔ በአቻ ውጤት ነበር ያለቀው።ከ 7ወር በኋላ አንደገና ለ2ተኛ ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ዳኞችን በአሰሠማነ ሁኔታ 7ኛው ዙር ላይ ማሸነፉ እና የ WBC ቀበቶውን ከ ዋይልደር መረከቡ ይታወሳል።
▪️በትላንቱ ፍልሚያ እስከ 18,000 የሚሆኑ ሰዎች ታዳሚ የሆኑ ሲሆን በአለማችን ከታዩ ምርጥ የከባድ ሚዛን ፍልሚያዎች አንዱ ነው ሲሉ የቦክሱ አፍቃሪያን ገልፀዋል።
▪️ፊውሪ በጨዋታው ላይ ሁለቴ ተንገዳግዶ የወደቀ ሲሆን ከዛ በመነሳት ሀይል የተቀላቀለበት ቡጢ ዋይልደር ላይ በማሳረፍ ዋይልደርም 11ኛው ዙር ላይ የፊውሪን ቡጢ መቋቋም ሳይችል ቀርቶ ተዘርሯል።
▪️ከጨዋታው በኋላ ፊውሪ በሰጠው አስተያየት ጥሩ ጨዋታ ነበር ጥሩ ሞክረሀል ብዬ ሰላም ልለው ነበር ፈቃደኛ አልነበረም ብሏል። ጥሩ ፍክክር አሳይቷል፣ፈትኖኛል ግን ፈጣሪ ከኔ ጋር ነበር ብሏል።
ሚካኤል ደጀኔ ።