የጣልያን ወደ አሸናፊነት መመለስ

የዩኤፍኤ ኔሽንስ ሊግ የደረጃ ጨዋታ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋን ጣልያን ከ ከዓለም ቁጥር አንዷ ቤልጂየም አገናኝቶ በባሬላ እና በዶሚኒኮ ግብ ታግዛ ጣሊያን ቤልጅምን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች ፡፡

 

ቤልጂየሞች በጉዳት ምክንያት ወሳኝ አጥቂያቸውን ሮሜሉ ሉካኩ እና ኤደን ሃዛርድን ሳያሰልፉ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት ፡፡ ባሳለፍነው ረዕቡ ያለመሸነፍ ጉዟቸውን በስፔን የተቋረጠባቸው ጣልያኖችም በበኩላቸው ወሳኞቹን ተከላካዮቻቸውን ቡኑቺን እና ቺሊኒን ወደ ሳይዙ ነበር  ሜዳ የገቡት  ፡፡

የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም ግብ ሲጠናቀቅ ፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ 46ኛው ደቂቃ ላይ የኢንተር ሚላኑ አማካኝ ኒኮላስ ባሬላ አስቆጥሮ ሀገሩን ጣልያን መሪ አደረገ ፡፡ በ65ኛው ደቂቃ ጣሊያኖች ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ዶሚኒኮ አስቆጥሮ ቤልጂየም 2 ለ 0 እንድትመራ ቢያስችልም ፡፡ በ86ኛው ደቂቃ በልጂየሞች በመልሶ ማጥቃት ኬትለር ከኬቨን ዲብሩዋይኔኬ የተቀበለውን ኳስ አስቆጥሮ ጨዋታው በጣሊያን አሸናፊነት ተጠናቆ ጣልያን በዩኤፍኤ ኔሽንስ ሊግ 3 ደረጃን በመያዛ አጠናቃለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.