ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 7ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤቶች።

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 7ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤቶች።
▪️የፓትሪክ ቪዬራው ክሪስታል ፓላስ ሌስተር ሲቲን አስተናግዶ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
▪የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር ከ አስቶን ቪላ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።ከ 2 ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ለተመለሰው የ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ‘ሆይቢዬ’ እና ‘ማት ታርጌት’ ራሱ ላይ አስቆጥሯል ኮርያዊው ሶን ሁንግ ሚን ደምቆ ባመሸበት ጨዋታ 2ቱነሰም ግቦች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
▪️ዌስት ሀም በሜዳው ለንደን ስቴዲየም በ አዲሱ አዳጊው ቡድን ብሬንትፎርድ 2-1 ተሸንፏል።የ ቶማስ ፍራንኩ ቡድን ዘንድሮ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል።

▪️በመጨረሻም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ ሊቨርፑል እና የ ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ የታክቲክ ሽኩቻ እና ስህተቶች ላለመስራት ጥንቃቄ’ን ቅድሚያ ያደረገ ጨዋታ ይዘው ወደሜዳ ገብተው ነበር።
ከእረፍት በፊት ጥሩ እንቅስቃሴ ከሙከራ ጋር ሲያደርግ የነበረው የ ፔፕ ቡድን ከእረፍት መልስ ተዳክሞ ታይቷል በአንፃሩ የ የርገን ክሎፑ ሊቨርፑል ከእረፍት መልስ ጠንክሮ ቀርቦ በ ሴኔጋላዊው ሳድዮ ማኔ አማካኝነት በ 59 ደቂቃ ቀዳሚ መሆን ችሎ ነበር።ከ 9 ደቂቃ በኋላ ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ ያመሸው ኢንግሊዝያዊው ፊል ፎደን የአቻነቷን ግብ ለክለቡ አስገኝቷል። በ 76ኛው ደቂቃ ግብፃዊው መሀመድ ሳላህ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ድንቅ ግብ አግብቶ ቡድኑ እንደገና መሪ ሚሆንበትን እድል አመቻችቶ ነበር ግን መሪነቱ ለ 3 ደቂቃ ብቻ ነው መቆየት የቻለው በ 79ኛው ደቂቃ ቤልጀማዊው ኬቨን ዴብራይን ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ማቲፕ ዲፍሌክት አርጎት አቻ የሆኑበትን ግብ አስቆጥሯል።
በዚህ መሰረት ጨዋታው 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

#ሚካኤል_ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published.