የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አመርቂ ድል ተጎናጸፈ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አመርቂ ድል ተጎናጽፈ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማዳጋስካር አቻውን 4-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አመርቂ ድል ተጎናጽፏል።

በዚህ ውጤት መሠረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከምድቡም 9 ነጥብ በመያዝ 1ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል ።

ዋልያዎቹ በጥሩ እንቅስቃሴ የመጀመሪያ አጋማሽን ሲጀምሩ ማራኪ ግቦችንም በ3ቱ የፊት መስመር አጥቂዎች ሲያስቆጥሩ አማኑኤል ገ/ሚካኤል በ19ኛ ደቂቃ ጌታነህ ከበደ በ34ኛው ደቂቃ እና አቡበከር ነስሩ በ41ኛ ደቂቃ 3ቱን የመጀመሪያ አጋማሽ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል ።

የማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው አስራ አምስት ደቂቃዎች ላይ አስደንጋጭ ሙከራን ማድረግ ቢችሉም ተክለማርያም ሻንቆ አምክኗል ።
በሁለተኛው አጋማሽ ማዳጋስካሮች ተጭነው ለመጫወት የሞከሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአንፃሩ ተረጋግቶ ኳስን ይዞ ለመጫወት ሞክሯል። በ86ኛው ደቂቃም ሽመልስ በቀለ 4ኛውን ግብ በማስቆጠር የብሔራዊ የቡድኑን አሸናፊነት አድምቆታል።
።ዋልያዎቹ በተከታታይ ሁለት የምድቡ ጨዋታዎች መረባቸውን ሳያስደፍሩ ወሳኝ ስድስት ነጥቦችን አሳክተዋል በተጨማሪም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ያለመሸነፍ ታሪካዊ ጉዟቸውን አስቀጥለዋል ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.