የወረደው ቦርሺያ ሞንቼግላድባህ በቡዳፔስት አስፈሪውን ማንችስተር ሲቲ ይገጥማል
የወረደው ቦርሺያ ሞንቼግላድባህ በቡዳፔስት አስፈሪውን ማንችስተር ሲቲ ይገጥማል
የቦርሺያ ሞንቼግላድባህ አሰልጣኝ ማርኮ ሮዜ ማንችስተር ሲቲን ከ2-0 መመራት ቀልብሶ ማሸነፍ በጣም ከባድ እንደሆነ ገልፀዋል ሲቲ ካለው የተጫዋቾች ጥራት እና የመጀመሪያው ጨዋታ 2-0 ማለቁ ነገሮችን እንዳይታሰቡ አርጓቸዋል ነገር ግን የወዳጅነት ጨዋታም አናረገውም እድል አለን ጥሩ ለመንቀሳቀስ እንሞክራለን ብለዋል። ቦርሺያ ሞንቼግላድባህ አቋሙ አሰልጣኙ በውድድር አመቱ መጨረሻ እንደሚለቁ እና ተቀናቃኛቸው ቦርሺያ ዶርትሙንድን እንደሚቀላቀሉ ካሳወቁ በኃላ ወርዷል አሁን በቡንደስሊጋው 10ኛ ላይ ሲገኙ 6 ጨዋታ ተከታታይ ተሸንፈዋል።
ማንችስተር ሲቲ በአንፃሩ ከማንቸስተር ደርቢው ሽንፈት ሳውዝ ሀምፕተንን እና ፉልሀምን በማሸነፍ ያገገመ ሲሆን ለዋንጫውም ትልቅ ግምት ይሰጣቸዋል።