ዝላታን ወደ ስዊድን ብሄራዊ ቡድን ተመለሰ

ዝላታን ወደ ስዊድን ብሄራዊ ቡድን ተመለሰ

ከ5 አመት ቆይታ በኃላ ብሔራዊ ቡድኑ ለአለም ዋንጫ ለማለፍ ወሩ መጨረሻ ላሉበት ጨዋታዎች የ39 አመቱ የኤሲ ሚላን አጥቂ በቡድኑ ተካቷል። አሰልጣኙም ያኒ አንደርሰን የተጫዋቹን መመለስ ዛሬ ያሳወቁ ሲሆን ዝላታንም በኢንስታግራም ገፁ የስዊድን ማልያን ለብሶ “የፈጣሪ መመለስ ” ሲል አወዛጋቢ ፅሁፉን ፅፏል።
ዝላታን በ2016 ከአውሮፓ ዋንጫ በኃላ ራሱን ሲያገል 116 ጨዋታዎችን አድርጎ 62 ጎሎችን ለሀገሩ አስቆጥሮ ነበር።
ተጫዋቹ በጡንቻ ጉዳት ከሜዳ ርቆ ቢቆይም በቀጣይ ሀሙስ ኤሲ ሚላን ከቀድሞ ቡድኑ ማንችስተር ዩናይትድ በሚያረገው ጨዋታ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.