28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዳሰሳ

28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዳሰሳ

ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ግስጋሴውን ፉልሀምን 3-0 በመርታት ሲቀጥል ማንችስተር ዩናይትድ እና ሌስተር ሲቲ ቦታዎቻቸውን አናት ላይ አስከብረው ቀጥለዋል ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ 0-0 በመውጣቱ ዌስትሀም ኤቨርተን ቶተንሀም እና አስቶን ቪላ 4ኛ መሆን ሚችሉበትን እድል አምክነዋል አስቶን ቪላ አቻ ሲወጣ ሌሎቹ ሁሉም ሽንፈትን አስተናግደዋል፡፡

ሌስተር ሲቲ አግቢ እና እድል ፈጣሪ ተጫዋቾቹን በጉዳት በማጣቱ ጎሎቹን ከየት ያገኛል ሚል ጥያቄዎች በሚነሱበት ሰአት ኪሊቺ ኢህያናቾ እነ ማዲሰን ባርነስ እና ጀስቲንን ባስረሳ መልኩ 3 ጎሎችን በማግባት የመጀመሪያ ሶስታውን ሰርቶ በአጠቃላይ ቡድኑ 5-0 እንዲያሸንፍ ረድቷል፡፡ተጫዋቹ ለ3 ወራት ያህል በፕሪምየር ሊጉ ጎል ሳያስቆጥር ዘልቆ ነበር ሼፍልድ ዩናይትድ ላይም ሶስታ በመስራት ባለፉት 8 ጨዋታዎች 7ኛ ጎሉን ለቡድኑ አስመዝግቧል፡፡

ቼልሲ አሁንም ለ12ኛ ጨዋታ ሽንፈት አላስተናገደም 10 ጨዋታዎች ላይ ጎል አልተቆጠረበትም 2 ግብም ነው በአጠቃላይ የተቆጠረበት ፡፡ቡድኑ አሁንም የተቸገረው ግብ ማግባት ላይ ቡድኑ ፊት መስመር ላይ ብዙ አማራጮች ቢኖሩትም በ12ቱ ጨዋታዎች 13 ጎሎችን ብቻ ነው ማስቆጠር የቻሉት፡፡ ዌስትሀም ኤቨርተን እና ቶተንሀም በመሸነፋቸው ምክንያት ቼልሲ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሁለቱም የለንደን ክለቦች ተስፋቸው ዩሮፓ ሊግ ነው አርሰናል እና ቶተንሀም በለንደን ደርቢ ትእይንታዊ የሆነ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ  ግሩም ግብ ፤ ፔናሊቲ እና ቀይ ካርድ ጨዋታውን አጅበውት ነበር፡፡ጨዋታውን አርሴናል 2-1 ማሸነፉ ደግሞ የቶተንሀምን የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ደረጃ ይዞ የመጨረስ አላማ አደናቅፏል በዚህም ምክንያት ሁለቱም ክለቦች  በቀጣይ አመት ቻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ  ያላቸው ተስፋ ዩሮፓ ሊጉን ማሸነፍ ሆኗል፡፡ሶን በጉዳት ተቀይሮ ወጥቶ ፤ ጥሩ አቋም ላይ የነበረው ጋሬዝ ቤልም በ55ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ወጥቶ ፤ ኤሪክ ላሜላ በቀይ ካርድ ተሰናብቶ ቡድኑ 10 ተጫዋች ሲኖረው ነበር ቶተንሀም ጥሩ መንቀሳቀስ የጀመረው ይህም ትልቅ ዋጋን አስከፍሏቸዋል ሀሪ ኬን በጨዋታው ግብ አግብቶ ከጨዋታ ውጪ ሲሆንበት የግብ አግዳሚም ሙከራውን የመለሰበት አጋጣሚ ነበር፡፡ደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ቶተንሀም በ45 ነጥብ 7ኛ ላይ ሲቀመጥ አርሰናል በ41 ነጥብ 10ኛ ላይ ይገኛል፡፡

ዛሬ ሊቨርፑል ከዎልቭስ ጋር  ከምሽቱ 5 ሰአት ጨዋታ ሲኖራቸው ሚያሸንፉ ከሆነ ካሉበት 8ኛ ደረጃ ወደ 6ኛ ደረጃ ከፍ ይላሉ ዎልቭስ ሚያሸንፍ ከሆነ ደግሞ ካሉበት 13ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ከፍ ይላሉ ስለዚህም ለሁለቱም ወሳኝ ጨዋታ ነው ሁለቱም ቡድኖች ዘንድሮ ደካማ ሆነው የመጡ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.