ሮናልዶ ለተቺዎቹ መልስ ሰጠ

ሮናልዶ ለተቺዎቹ መልስ ሰጠ

ጁቬንቱስ ከቻንፒየንስ ሊግ መድረክ መሰናበቱን ተከትሎ ትችት በዝቶበት የነበረው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርሲቲያኖ ሮናልዶ ጁቬንቱስ ከካግሊያሪ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመጀመሪያ አጋማሽ ሶስታ በመስራት ለተቺዎቹ መልስ ሰጥቷል፡፡በሰርዲንያ በተደረገው ጨዋታ በ10 ኛው ደቂቃ በጭንቅላት በ25ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና በ31ኛው ደቂቃ በግራ እግሩ ኳስ እና መረብን በማገናኘት ሙሉ ሶስታ ሰርቷል ይህም 57ኛ ሶስታው ነው፡፡ሴሪ ኤውን ሚመራው ኢንተር ሚላን በ10 ነጥብ ልዩነት ሊጉን እየመራ ሲሆን 1 ቀሪ ጨዋታም አላቸው ፤ ተከታዩ ኤሲ ሚላን በናፖሊ 1-0 መሸነፉን ተከትሎ የዋንጫ ግስጋሴው የተገታ ይመስላል ከጁቬንቱስም በ1 ነጥብ ብቻ በልጠው 2ኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡

ሮናልዶ የሴሪ ኤ ኮኮብ ግብ አግቢነቱን በ23 ግቦች ሲመራ ካግሊያሪ ላይ ያስቆጠራቸው 3 ግቦች በአጠቃላይ ያገባቸውን ጎሎች ብዛት 770 አድርሰውታል በዚህም የታላቁን ፔሌ 767 ህጋዊ ግቦች መብለጥ ችሏል በዚህም የአለማችን ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኗል፡፡ከጨዋታውም በኋላ ለፔሌ ያለውን አድናቆት የገለጸ ሲሆን ከዚህ በፊት 757 ጎል ላይ ፔሌን በልጦታል ሲባል ሌላ 10 ጎሎች አሉት በመባሉ አሁን አስሩን አግብቶ 770 በማድረሱ ደስታውን ሊገልጽ እንደፈለገም ተናግሯል፡፡ጨንሮም ለዚህ እደርሳለው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ለዛም የረዱኝን የቡድን አጋሮቼን አሰልጣኞቼን ጠጋጣሚዎቼን ከሁሉም በላይ ደግሞ ቤተሰቦቼን እና የቅርብ ጓደኞቼን አመሰግናለሁ ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.