በህይወቴ ጨለማ የሆነ ቦታ ላይ ነበርኩ

በህይወቴ ጨለማ የሆነ ቦታ ላይ ነበርኩ የዘመኔን ትልቁን ሽንፈት ነበር ያስተናገድኩት
ቶማስ ቱሄል በቻምፒየንስ ሊጉ ፒኤስጂን እየመሩ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በማንችስተር ዩናይትድ የደረሰባቸውን ሽንፈት አይረሱትም።በ2019 የውድድር ዘመን ኦሊጉናር ሶልሻየር በኦልድትራፎርድ 2-0 ሽንፈትን አስተናግዶ ነበር ወደ ፓርክ ዴ ፕሪንስ ያመሩት ብዙ ተጫዋቾችንም በጉዳት አጥተው ነበር ነገሮች የተገላቢጦሽ ሆነው በመጨረሻ ሽርፍራፉ ደቂቃዎች አሸንፈው ከውድድር ውጪ አደረጓቸው።
አሁን ደግሞ ቱሄል የሰሜን ለንደኑን ቼልሲ ይዘው 4ቱ ውስጥ ሆኖ ለመጨረስ ሚያስችላቸውን ፍልሚያ በሊጉ ሰንጠረዥ 2ኛ ደረጃ ላይ ሚገኘውን የኦሊጉናር ሶልሻየር ማንችስተር ዩናይትድ ይገጥማሉ።
” እውነቱን ልንገራችሁ በጊዜው ለ2 ቀን ያህል መጥፎ ስሜት ውሰጥ ነበርኩ ከሰዎች መግባባት አቅቶኝ ነበር ከሽንፈቱ ውጪም ስለምንም ማሰብ ተስኖኝ ነበር” ይላሉ ቱሄል የ2019ኙን ሽንፈት ሲያስታውሱ አሁን ያን ታሪክ ለመገልበጥም እንጫወታለን ፉክክሩን እንወደዋለን ማሸነፍም እንፈልጋለን ለሱም እንታገላለን ከእሁዱም ጨዋታ ይሄን ነው ምንጠብቀው ብለዋል።
በቼልሲ ቡድን ውስጥ ከቲያጎ ሲልቫ ውጪ ሁሉም ብቁ ናቸው።ስለ ካይ ሀቨርትዝም በሰጡት አስተያየት ጉዳት እንጂ ትልቅ ብቃት ያለው ተጫዋች ነው በዚህ ሰአት በ9 ቁጥር ወይም 10 ቁጥር ቦታ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደርጋል ማቀበልም መጨረስም ላይ ጎበዝ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.