አውባሜያንግ እና ቡካዮ ሳካ በግሪክ አርሰናልን ወደ ቀጣዩ የዩሮፓ ሊግ ዙር አሳፉ

አውባሜያንግ በግሪክ አርሰናልን ወደ ቀጣዩ የዩሮፓ ሊግ ዙር አሳለፈ

ፒር ኤምሪክ አውባሜያንግ 2 ጎሎችን ለቡድኑ በማስቆጠር ወደ ቀጣይ ዙር እንዲያልፉ ረድቷል አርሰናል ከ ፖርቹጋሉ ቤኔፊካ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታው 1-1 እንዳለቀ ሚታወስ ሲሆን አርሰናል በመልሱ ጨዋታ 3-2 በማሸነፍ በድምሩ 4-3 በሆነ ውጤት ወደ 16ቱ ማለፉን አረጋግጧል፡፡

በእንግሊዝ ባለው የጉዞ እገዳዎች ምክንያት የፖርቹጋሉ ቡድን ወደ ለንደን ለመምጣት በለመቻሉ ጨዋታው በግሪክ አቴንስ የኦሎምፒያኮስ እስታዲየም ካራኢስካኪስ ነበር፡፡ ጋቦናዊው አጥቂ አውባሜያንግ የጨዋታውን የመጀመሪያ ጎል ለአርሰናል በ20ኛው ደቂቃ ከቡካዮ ሳካ የተሻገረለትን ድንቅ ኳስ በበረኛው ላይ ቺፕ በማረግ አስቆጥሮ 1-0 መምራት ችለው ነበር ፡፡ሆኖም በ43ኛው ደቂቃ ዳኒ ሴባዮስ ከፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ ዊግል ላይ በሰራው ጥፋት የተሰጠን የቅጣት ምት ዲያጎ ጎንካልቬዝ ከመረብ በማገናኘት አቻ ሆነው እረፍት ወጥተዋል፡፡

ከእረፍት መልስም ተጭነው መጫወት የቻሉት ቤኔፊካዎች በ61ኛው ደቂቃ በራፋ ሲልቫ  2ኛ ጎል ጨዋታውን መምራት ችለዋል፡፡ይህም ጨዋታውን አርሰናል ለማለፍ በቀሩት 30 ደቂቃዎች 2ጎሎችን ማስቆጠር ግዴታቸው ነበር ይህንንም ማሳካት ችለዋል ከዊሊያን ያገኘውን ኳስ ኬራን ቲርኒ አስቆጥሮ አቻ ማድረግ ቻለ፡፡ከዚ በኋላ አርሰናል ተቀዛቅዞ ቢታይም በ87ኛው ደቂቃ በድጋሜ ቡካዮ ሳካ ያሻገረለትን ኳስ በጭንቅላት ገጭቶ አስቆጥሮ 3-2 አሸንፈው እንዲወጡ አድርጓል፡፡

የጨዋታው ኮከብ ሆኖ የተመረጠው ግን ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱን የቀጠለው ታዳጊ ቡካዮ ሳካ ነው ፡፡ በጨዋታው ሁለት ጎል የሆኑ ኳሶችን ለአውባሜያንግ ማቀበል ችሏል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.