” ጦርነት ላይ ሚያሸንፉት በጣም ብዙ ወታደር ያላቸው አይደሉም…… “

አትሌቲኮ ማድሪድ ከቼልሲ ይሄ ተጠባቂ ጨዋታ በብዙ መንገድ እየተተነተነም ነው አንደኛው ነገር የክለቦቹ የአሰልጣኞች ቅጥር ባህሪይ ደጋግሞ ይነሳል ። ዲያጎ ሲምኦኔ በ2011 አትሌቲኮን ከያዘ በኃላ ባሉት አመታት ቼልሲ 9 አሰልጣኞችን ቀይሯል ከነዚህም ውስጥ ጆዜ ሞሪንሆ ፣ ካርሎ አንቾሎቲ እና አንቶኒዮ ኮንቴ ፕሪምየር ሊጉን አንስተው ነው የተባረሩት በቅርቡም ፍራንክ ላምፓርድ ከ220 ሚልየን ፖውንድ በላይ አስወጥቶ ቡድኑ ውጤት ሲርቀው አሰናብተውታል።ይህም ቼልሲን ልዩ ክለብ ያረገዋል አብራሃምኦቪች ክለቡን በያዙበት 18 አመታት በእንግሊዝ እንደ ቼልሲ ብዙ ዋንጫ ያሳካ የለም ይህም ብቸኛው ቻንፒየንስ ሊግን በ2012 ለንደን ያመጣውም ክለብ ያረገዋል። ግን ይህም ሆኖ ይሄ የለውጥ ብዛት በአውሮፓ ቋሚ አቋም እንዳያሳይ ያረገዋል ክለቡን ይላሉ ተንታኞች በ2013/14 በአትሌቲኮ ማድሪድ ከግማሽ ፍፃሜው ከወጡ በኃላ ጥሎ ማለፉን አልፈው አያውቁም።


በእንፃሩ የገንዘብ አቅሙ ከቼልሲ ማይወዳደረው አትሌቲኮ 2 የቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜዎችን ደርሶ በከተማ ተቀናቃኙ በጭማሪ ሰአት ተቆጥሮበት እና በፔናሊቲ ቢያጣም ቡድኑ ቋሚ የቻምፒየንስ ሊግ ተፋላሚ ሆኖ ቆይቷል 2 የሩብ ፍፃሜ ፣ 1 የግማሽ ፍፃሜን እና ኢሮፓ ሊግን ማሸነፍ ችሏል።

ሲሚኦኔ እና አትሌቲኮ የሀብታም ክለቦች ጡንቻ ቢጫናቸውም ሁሌም ወድቀው አይቀሩም ይነሳሉ ያንሰራራሉ በ2013/14 ላሊጋውን ካነሱ በኃላ ተጫዋቾቻቸውን ካስኮበለሉት መሀል ደግሞ ቼልሲ አንዱ ነው ዲያጎ ኮስታን እና ፌሊፔ ሉዊስን በመግዛት ከዛም በኃላ በተለያዩ ጊዜያት ኮኮቦቻቸውን ተነጥቀዋል ግን ትልቅ ትርፍ ያገኙባቸው ዝውውሮችም ነበሩ ራዳሚል ፋልካኦ ፣ አርዳ ቱራን ፣ አንቶኒ ግሪዝማን ፣ ሉካስ ኸርናንዴዝ ፣ ሮድሪጎ እና ቶማስ ፓርቴ በረብጣ ሚልየኖች ተሽጠው ቡድኑ ተጠቅሟል።

” ጦርነት ላይ ሚያሸንፉት በጣም ብዙ ወታደር ያላቸው አይደሉም ያሏቸውን በአግባቡ ሚጠቀሟቸው ናቸው ” በአንድ አጋጣሚ ስለ አትሌቲኮ እና ትልቅ ሚባሉትን ቡድኖች ስለመፈተኑ ሲጠየቅ ሰምኦኔ የተናገረው ነው ። አሁን ሁሉም አትሌቲኮን መግጠም ይፈራል ወኔአቸው እና ታጋይነታቸው ለማንም ያስፈራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.