አትሌቲኮ ማድሪድ ከቼልሲ ዛሬ የሚደረግ የቻምፒየንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

አትሌቲኮ ማድሪድ ከቼልሲ ዛሬ የሚደረግ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ሲሆን አሰልጣኞቹ ስለጨዋታው የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛል። ቶማስ ቱኼል ሉዊስ ስዋሬዝን ኡራጋያዊው አጥቂ ያልተጠበቀ ዝውውሩን ወደ ስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ከማድረጉ በፊት ለፒኤስጂ ለማስፈረም ሞክሮ እንደነበር ተናግሮ አሁን ቀኑ ደርሶ ቱኼልም ቼልሲ ገብቶ በቻምፒየንስ ሊጉ 16ቱ ውስጥ ፍልሚያ ያረጋሉ ሱዋሬዝ አስፈሪ አቋም ላይ ሆኖ አትሌቲኮን የላሊጋው መሪ አድርጎ ቱኼልም በጥሩ አጀማመር ቼልሲን እየመራ ባረጋቸው በ7 ጨዋታዎች ሳይሸነፍ በቻምፒየንስ ሊጉ ልምድ ያለውን የዲያጎ ሲምኦኔን ቡድን ዛሬ ቡካሪስት ናሽናል አሬና ላይ 5 ሰአት ላይ ይጫወታሉ።
ዛሬ ትልቅ የአዕምሮ እና የጉልበት ፈተና ይጠብቀናል ያሉት ቱኼል አትሌቲኮ ልምድ ያለው የተደራጀ ቡድን ልምድ ባለው ከባድ አሰልጣኝ ሚመራ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ይጠብቀናል ታጋይ ቡድን እንደሆነ ማንም ያውቃል ። የዘንድሮው አትሌቲኮ ደግሞ በማጥቃቱ በኩል የተሻለ ሆኖ የመጣ ነው።


ዲያጎ ሲምኦኔ በበኩሉ ሉዊስ ስዋሬዝ የጎል ማግባት ተሰጥኦውን እንዲጠቀም ምኞቱ እንደሆነ ገልፆ እሱ ጎል አነፍናፊ ነው ስሙ እና ዝናውም ለተጋጣሚዎች ያስፈራል ሲል አሞካሽቶታል ስዋሬዝ በ24 ጨዋታዎች 16 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ሲምኦኔ ቱኼልንም ጥሩ ሚጫወት ጥሩ ቡድን ሰርቷል ጎበዝ አሰልጣኝ ነው እኛም ለጨዋታው ተዘጋጅተናል ብሏል።

ሁሌም ቼልሲ እና ስዋሬዝ ሲነሱ ማይረሳው ሱዋሬዝ ሊቨርፑል እያለ ብራንስላቭ ኢቫኖቪችን የነከሰበት አጋጣሚ ነው ከዛም ክስተት በኃላ ይህ መርሀ ግብር ከወትሮውም ሞቆ ነበር ስለዚህም ጉዳይ ተነስቶ የተጠየቁት ቱኼል ያለፈው አልፏል ከድሮ ቁርሾ አሁን ላይ ማተኮር ያዋጣናልም ብለዋል።

One thought on “አትሌቲኮ ማድሪድ ከቼልሲ ዛሬ የሚደረግ የቻምፒየንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.