በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 11 ኛ ሳምንት ዛሬ ረፋድ በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀዲያ ሆሳዕና 1ለ 1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
ዳዋ ሁቴሳ ለሃዲያ ሆሳዕና ግቧን ሲያስቆጥር በተመሳሳይ ሄኖክ አዱኛ ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ሀዲያ ሆሳዕና በ19 ነጥብ እና በስድስት የጎል ልዩነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ሀድያ ሆሳዕናን በመከተል በ18 ነጥብ እና በሰባት የጎል ልዩነት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

One thought on “በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published.