ማንችስተር ዩናይትድ በጎል ተንበሽብሿል

ቀያይ ሴጣኖቹ በጊዜ ተጫዋቻቸውን በቀይ ካርድ ባጡት ሳውዝሀምፕተን ላይ ዘጠኝ ጎሎችን በማስቆጠር ሶስት ነጥብ አሳክተዋል ።
• ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ 46 ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ለመሆን በቅቷል ።
• ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዓመት በመጀመሪያ አጋማሽ ከ ሶስት በላይ ጎሎችን ሲያስቆጥር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ።
• ለረጅም ጊዜ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ሉክ ሻው ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ሲችል በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።
• ኤዲሰን ካቫኒ በሊጉ 668 ደቂቃዎችን ብቻ መጫወት ሲችል አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ።

• ኤዲሰን ካቫኒ በ ኦልትራፎርድ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ።

• ዩናይትዶችን መሪ ያደረገች ግብ ማስቆጠር የቻለው አሮን ዋን ቢሳካ በ ኦልትራፎርድ ያስቆጠረው የመጀመሪያ ግቡ መሆኑ ተገልጿል ።

• ማርከስ ራሽፎርድ በሊጉ ባደረጋቸው ሀያ ሁለት ጨዋታዎች በአስራ ሶስት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል ።

• ራሽፎርድ 83ኛ ጎሉን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ይህም ከ ኤሪክ ካንቶና በላይ አድርጎታል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.