ማርሴይ አሰልጣኙን አሰናበተ

በተለያዩ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ኦሎምፒክ ማርሴይ አሰልጣኛቸውን አንድሬ ቪያስ ቧስን ማሰናበታቸውን አሳውቀዋቀል ።
• አንድሬ ቪያስ ቧስ ከሰዓታት በፊት በትላንትናው ዕለት ከተገዙት ተጫዋቾች መካከል የ ሴልቲኩ ኦሊቨር ንቻም የእርሱ ፍላጎት አለመሆኑ እና በመካከላቸው ልዩነት መኖሩን ተከትሎ መልቀቂያ ከምሳ ሰዓት በኋላ አስገብቶ ነበር ።
• አንድሬ ቪያስ ቧስ እንዳሳወቀው የተጫዋቹን ግዢ ጠዋት ላይ ከመገናኛ ብዙሀን እንደሰማ እና ተጫዋቹን እንደማይፈልገው አስቀድሞ መናገሩን ገልጿል ።
• አንድሬ ቪያስ ቧስ አስከትሎም ከክለቡ ምንም አይነት ነገር ብርን ጨምሮ እንደማይፈልግ እና ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግም ገልፆ ነበር ።
• ማርሴይ በሊጉ ቀሪ ጨዋታዎች ቢኖሯቸውም ካለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች አንዱን ሲያሸንፉ በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.