ኢትዮጲያ ቡና ምንተስኖት ከበደን አስፈርሟል
ለአዳማ እና ለመከላከያ የተጫወተው ምንተስኖት ከበደ (አፍሪካ) ለኢትዮጵያ ቡና ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን የውል ስምምነት ፈርሟል።
ምንተስኖት ለመቐለ 70 እንደርታ ፈርሞ የነበረ ቢሆንም ክለቡ በፀጥታ ችግር በውድድሩ መሳተፍ አለምቻሉን ተከትሎ ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ሊዘዋወር መቻሉን ኢትዮጲያ ቡና እስፖርት ክለብ ፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።
በያዝነው የ2013 የውድድር ዘመን በትግራይ ክልል የሚገኙ ክለቦች በፕሪሜር ሊግ መሳተፍ አለመሻላቸውን ተከትሎ ለትግራይ ክልል ላሉ ክለብ ተጫዋቾች በተሰጠው ዕድል መሰረት መቐለ 70 እንደርታ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ወደፈለጉት ክለብ የመዛወር እድል እንዳላቸው ተነግሯል። ምንተስኖትም ይሄንን እድል ከተጠቀሙ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ ነው።
laregond 1aedd1d5d3 https://wakelet.com/wake/a27Y3CJ41gF0RUS2BiLQy