መቐለ 70 እንደርታ ጉዳይ ወደ ካፍ አምርቷል

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው መቐለ 70 እንደርታ ጉዳይ መፍትሄ ያስገኛል የተባለ ደብዳቤ ወደ ካፍ ተልኳል።

የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን መደልደሉ ይታወቃል። በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ከኅዳር 18 – 20 ባሉት ቀናት ከሜዳው ውጭ ግብፅ አልያም ቱኒዚያ ላይ የሚጫወት መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። የመልሱን ጨዋታ ከአንድ ሳምንት በኃላ በሜዳው ከኅዳር 25-27 ባሉት ቀናት እንደሚያደርግ መርሐግብር መውጣቱ ይታወቃል። ሆኖም አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር መቐለ 70 እንደርታን በጨዋታው ላይ እንዲካፈል ለማድረግ ለካፍ ደብዳቤ ተልኳል ሲል ©ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.