ሎዛ አበራ በቢቢሲ የዓለማችን 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ውስጥ ተካተተች።

ኢትዮጵያዊቷ የፊት መስመር ተሰላፊ ሎዛ አበራ በተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ዓለምአቀፍ ትኩረት አግኝታለች።

የእንግሊዙ የሚዲያ ተቋም ቢቢሲ እንደአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ 2013 ጀምሮ ዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚላቸውን 100 እንስቶች በየዓመቱ ይፋ ያደርጋል። እንስቶቹ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ተሰማርተው በማህበረሰባቸው ውስጥ ቢፈጥሩት ከፍ ያለ ተፅዕኖ መነሻነት ነው በተቋሙ ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱት።

በዚህ መሰረት ቢቢሲ የ2020 ተፅዕኖ ፈጣሪ ያላቸውን ሴቶች ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያዊቷ እግርኳሰኛ ሎዛ አበራንም አካቷታል። በቅርቡ በማልታ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጫወት ፊርማዋን ያኖረችው ሎዛ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች በውጪ ሀገራት ሊጎች በከፍተኛ ብቃት መጫወት እንደሚችሉ ምስክር መሆን በመቻል ለወጣት ተጫዋቼች አረዓያ መሆን ስለመቻሏ ብዙዎች ይመሰክራሉ። አሁን ደግሞ ለዚህ ጥንካሬ የተላበሳ የእግርኳስ ህይወቷ ዓለምአቀፍ ሽፋንን አግኝታለች።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.