ሎዛ አበራ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ልትቀላቀል መሆኑ ተሰማ ፡፡

በማልታ ሊግ የደመቀችው ሎዛ አበራ የአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛውን ኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ለመቀላቀል ተስማምታለች ሲል ሀትሪክ ስፖርት አስታውቋል፡፡

ሴናፍ ዋቁማን ከአዳማ ከተማ ለማስፈረም በተደረገው ትንቅንቅ በመከላከያ ተረተው እጅ የሰጡት ኢትዮጲያ ንግድ ባንኮች በሎዛ ከመከላከያ የገጠማቸውን ትግል አሸንፈው በእጃቸው ያስገቡ ሲሆን ልደታ ቤ/ክ አካባቢ በሚገኘው ዛጉኤል ህንጻ ላይ ባለው የመሠብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ በሚኖረው የፊርማ ስነስርአት በይፋ ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል፡
ሎዛ አበራ ከደደቢትና ከአዳማ ከተማ ጋር የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ከማልታው ቢኪርካራ ጋር የማልታ ሊግን በድል ስታጠናቅቅ በግሏ በኮከብ ግብ እስቆጣሪነት የጨረሰች ውጤታማ አጥቂ ናት፡፡
እስከ 90ሺ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ሊከፈላት የሚችለው ሎዛ በኢትዮጲያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ትደምቃለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.