ከ17ዓመት በታች አዲሱ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በይፋ ታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታህሳስ ወር በሚጀመረው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያ መድን የቀድሞ ከ17በታች እና የአሁን ከ20ዓመት በታች አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ በአንድ አመት ውል አስፍርሟል።

አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ መድን ከ17ዓመት በታች ቡድን በ2011 የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆን ማድረጋቸው ይታወሳል።

አሰልጣኙ በሴካፋ ውድድር የተሻለ እና ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን እንዲሰሩ ግዴታ ውስጥ ገብተዋል ሲል ፌዴሬሽኑ በፌስቡክ ገፁ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.