ትናንት በአውሮፓ አምስቱም ታላላቅ ሊጎች ተደርገዋል

ትናንት በአውሮፓ አምስት ታላላቅ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ቶተንሀም ብራይተንን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ አርሰናል ማንችስተር ዮናይትድን አንድ ለ ዜሮ በመርታት ድል የቀናቸው ሲሆን ሌሎች የሊጉ ክለቦች ኒውካስትል እና ሳውዝ ሀፕተንም የድል ባለቤት ሁነዋል፡፡

በፈረንሳይ ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ሞናኮ በርዶንን አራት ለዜሮ ኒስ አንገርሰንን ሶስት ለዜሮ መርታት ችለዋል እንዲሁም ሬምስ ፣ ሜትዝ እና ሞን ፔሌ በሊጉ ሌሎች ባለድል መሆን ችለዋል፡፡

በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ስድስተኛ ሳምንት ባየር ሌቨርኩሰን ፍራይ በርግን አራት ለ ዜሮ በማሸነፍ የሶስት ነጥብ ባለቤት መሆን ሲችል ወልፍስበርግ እና ኸርታ በርሊን ባደረጉት ጨዋታ ደግሞ አቻ በመውጣት ውጤት ተጋርተዋል ፡፡

እንዲሁም በጣልያን ሴሪያ ስድስተኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ጁቬንቱስ ስፔዚያን አራት ለ አንድ ያሸነፈ ሲሆን ኤስ ሚላን ዩዴኒዜን ፣ ኤስ ሮማ ፊዮሬንቲናን ፣ ላዚዮ ቶሪኖን  ፣ሳሎል  ናፖሊን በመርታት በሊጉ በተደረገው ጨዋታ የድል ባለቤት ሁነዋል፡፡

በስፔን ላሊጋ ስድስተኛ ሳምን በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሪያልሲዳድ እና ሪያል ቤትስ ድል የቀናቸው ሲሆን ግራናዳ ከ ሌቫንቴ ቫሌንሽያ ከ ሄታፌ ደግሞ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.