መድፈኞቹ ቀያይ ሰይጣኖችን በሜዳቸው በመርታት ድል ቀንቷቸዋል
እ.ኤ.አ ከ2014 በኋላ በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ግብ ማስቆጠር ያልቻለው ፔር ኤምሪክ ኦቦምያንግ በሁለተኛ አጋማሽ ያስቆጠራት የፍፁም ቅጣት ምት ግብ አርሴናል ከኦልድ ትራ ፎርድ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲመለስ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ፡፡
በተቃራኒው ቀያይ ሰይጣኖች በዘንድሮው የዉድድር ዓመት በሜዳቸው ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት ሲቸገሩ ተስተውሏል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሴናል እ.ኤ.አ በ2006 የውድድር አመት በኢማኑኤል አዲባየር ብቸኛ ግብ በፕሪምየር ሊጉ በኦልድ ትራ ፎርድ አሸንፎ የወጣ ቢሆንም ከ14 ዓመታት በኋላ ግን ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ የድል ባለቤት
ማንችስተር ዮናይትዶች በዘንድሮው የውድድር ዓመት ካደረጓቸው ስድስት ጨዋታዎች ማግኘት የቻሉት ሰባት ነጥቦችን ብቻ ነው፡፡