ባርሴሎና ከ ጁቬንቱስ ዛሬ ምሽት በሚያደርጉት ጨዋታ አርቱር የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒ ይገጥማል።

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በትላንት እለት 3ኛ ዙር የኮቪድ ምርመራ አድርጎ ፖሰቲቭ ሆኗል። ይህንን ተከትሎ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር በድጋሚ የሚገናኝበትን እድል አቷል።

ማቲያስ ዴላይት የትከባ ሰርጀሪ ካደረገ በኋላ ቡድኑን ለመቀላቀል ከጫፍ እንደደረሰ ተነግሯል። ነገር ግን በባርሴሎና ጨዋታ የማናየው ይሆናል።በተቃራኒዉ ፊሊፕ ኩቲኖ በጡንቻ ጉዳት ለዛሬው ጨዋታ እንደማይደርስ አሰልጣኙ ተናግረዋል።

የ17አመቱ ፔድሪ በኤልክላሲኮ ባሳየው አቋም ለዚህ ጨዋታ ሊጠቀሙት ይችላሉ ተብሎም ይጠበቃል ፡፡

አሌክስ ሳንድሮ እና ሊዮናርዶ ቦኑቺ አሁንም ጉዳት ላይ ይገኛሉ ይህም የባለሜዳዎች የተከላካይ ክፍል እንደላላ የሚያሳይ ሲሆን የባርሴሎናዉ ጄራርድ ፒኬ ባለፈው የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቀይ ካርድ ማየቱን ተከትሎ በቅጣት በዚህ ጨዋታ አናየውም።

አድሪያን ራቢዮት እና ሮድሪጎ ቤንታኩር የጁቬንቱስ  በመሃል ክፍሉ አማራጭ ተጫዋቾች ሲሆኑ በባርሳ በኩል ደግሞ ትሪንካዎ እና ኦስማን ዴምቤሎም  ሌሎች አማራጭ ተጫዋቾች ናቸው።

በተጨማሪም አሮን ራምሲ እና ዴጃን ኩሉሴቪስኪ ሊጣመሩ ይችላሉ። ሞራታ በዚህ ጨዋታ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.