በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ባየር ሙኒክ እና ሊቨርፑል ድል ተቀዳጅተዋል ፡፡

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ ከተሞች ተካሄደዋል፡፡

በምድብ አንድ ከሜዳው ውጭ ከሎኮሞቲቭ ሞስኮ የተጫወተው ባየር ሙኒክ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ አትሌቲኮ ማድሪድ ሳልዝበርግን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

በምድብ ሁለት የተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡

ሻካታር ከኢንተር ሚላን ያለምንም ጎል እንዲሁም ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህ ከሪያል ማድሪድ 2 አቻ ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡

በምድብ ሶስት ፖርቶ ኦሊምፒያኮስን 2 ለ 0 እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ማርሴይን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡

በምድብ አራት ደግሞ አታላንታ ከአያክስ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በሜዳው ሚዲቲላንድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ደግሞ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ቡድኖች ደግሞ ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ጁቬንቱስ ከ ባርሴሎና ፣ ማን ዩናይትድ ከ RB ሌፕዚሽ የሚያደርቡት ጨዋታ ተጠባቂዎች ናቸዉ ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.