ፈረሰኞቹ ልምምዳቸውን ለመጀመር ቢሾፍቱ ገቡ::

ፈረሰኞቹ የኮቪድ-19 በሽታ ለወራት አቁዋርጦት የነበረውን ልምምዳቸዉን ከአዲሱ አሰልጣኛቸዉ ጋር ለመጀመር ቢሾፍቱ መግባታቸዉን በድረ ገፃቸዉ አሳወቋል፡፡

ሁሉም የቡድኑ አባላት በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ለ45 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን ልምምዳቸውን በጥብቅ ዲሲፕሊንና ስነ ምግባር እንዲያከናውኑም ከስራ አመራር ቦርዱ እጅግ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ የልምምድ ሜዳ፣የማረፊያና የመመገቢያ ክፍሎች እንዲሁም ሌሎች በአካዳሚው የሚገኙ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ክፍሎች የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩት ያወጧቸውን መሰረታዊ የጤና መመሪያዎችና ፕሮቶኮሎች መነሻ በማድረግ ግምገማ ተደርጎላቸው አስተማማኝ መሆናቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.