የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ
በኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ6ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ዛሬ ጥቅምት 14 ቀጥለው ሲውል ምሽት 1:30 ላይ የሳልሻየሮቹ ማንቸስተር ዩናይትዶች በሜዳቸው የፍራንክ ላምፓርዱን ቼልሲ የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ከወዲሁ ቀልብ ስቧል ።
ቼልሲዎች ከዝውውር እገዳው በኋላ በርካታ ትልልቅ ተጫዋቾች ቢያስፈርምም በርካታ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ተስኗቸዋል ።
ማንቸስተር ዩናይትዶች ደግሞ ከቶተንሀሙ አሰቃቂ ሽንፈት በኋላ ፒኤስጂ እና ኒውካስትልን አሸንፈው ነው ለዛሬው ፍልሚያ የተዘጋጁት ።
ቼልሲዎች በኦልድትራፎርድ ባደረጉዋቸው ያለፉት 7 ሊግ ጨዋታዎች ምንም ማሸነፍ አልቻሉም ። በአራቱ አቻ ሲለያዩ በሶስቱ ሽንፈትን ቀምሰዋል ።
ማንቸስተር ዩናይትዶች አዳዲሶቹ ፈራሚዎቻቸውን አሌክስ ትለስ እና ኤዲሰን ካቫኒ ያሰለፋሉ ተብለው ሲጠበቅ በቼልሲዎች በኩል ክርስቲያን ፑልሲች እና ቲያጎ ሲልቫ ለጨዋታው ብቁ መሆናቸው ተገልጿል ።
የፍራንክ ላምፓርዱ ስብስብ በጉዳት ቢሊ ጊልሙር እና ግብ ጠባቂው ኬፓ አሪዛባላጋ ከዛሬው ስብስብ ውጪ ሲያደርግ በማንቸስተር ዪናይትድ በኩል አንቶኒ ማርሻል ከቶተንሀም ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ቀይ ካርድ ስለተመለከተ በዛሬው ጨዋታ የማይሰለፍ ሲሆን ኤሪክ ቤይሊ እና ጄሴ ሊንጋርድ በጉዳት በዛሬው ምሽት ለክለባቸው ግልጋሎት እንደማይሰቱ ታውቋል ።