የአትሌቲኮ ማድሪድ እና የሌፕዚግ ጨዋታ አስገራሚ እውነታዎች

የጀርመኑ አርቢ ሌፕዚግ ዕድሜው 11 አመት ብቻ ነው በዚህ 11 አመት ውስጥ 4 የጀርመን ሊግ ውድድሮችን ያለፈ ሲሆን ባለፈው አመት በቡንደስሊጋው ሶስተኛ ወቶ ሻምፒየንስ ሊግ የተሳተፈ ሲሆን ትናንት ምሽትም አትሌቲኮን በመጣል ለመጀመርያ ጊዜ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል

የትናንት ማታው ጨዋታ ለሌፕዚግ የመጀመርያው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን በቻምፒየንስ ሊግ ለመጀመርያ ጊዜ የስፔን ክለብንም ያገኙበት ጨዋታ ነበር

አትሌቲኮ ማድሪድ በሻምፒየንስ ሊጉ ሮናልዶን ባልገጠመበት ጫወታ ከጥሎ ማለፍ ፉክክር ውጪ ሲሆን ለመጀመሪያ ግዜ ሆኗል

የማሸነፊያውን ጎል ያስቆጠረው ቴይለር አዳምስ ለሌፕዚግ ያስቆጠረው የመጀመሪያ ጎሉ ሲሆን በሻምፒየንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ ላይ ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው አሜሪካዉ ተጫዋችም ሆኗል

የሊፕዚጉ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግሌስማን የተወለደው በ1987 ሲሆን የአትሌቲኮ ማድሪዱ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሚዮኒ እንደተጫዋች የመጀመርያ ጨዋታውን ያረገው ደግሞ በ1987 ነበር

በመጨረሻም በወጣቱ አሰልጣኝ የሚመሩት ሌፕዚጎች በውድድሩ ጥሩ ልምድ ያላቸውንና ቻምፒዮኖችን ጥለው ያለፉትን አትሌቲኮዎች በመጣል ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በግማሽ ፍጻሜው ማክሰኞ ፒኤስጂን የሚገጥሙ ይሆናል።

 

 

ፍሬው ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published.