የሪያል ማድሪድ የምን ጊዜም ድንቁ ግብ ጠባቂ ኤከር ካሲያስ ትናንት ከእግር ኳስ መለያየቱን ይፋ አደረገ ።

ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫን ማሳካት የቻለው ኤከር ካስያስ ለሎስ ብላንካዎቹ ሪያል ማድሪዶች 700 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል ።

ካሲያስ በቲውተር ገፁ እንዳስታወቀው ከሆነ “ዛሬ በስፖርት ህይወቴ በጣም አስፈላጊ እና በጣም አስቸጋሪ ከሆኑት ቀናቶች ውስጥ አንዱ ነው ፣ እግር ኳስንም ለመሰናበትም ጊዜው አሁን ነው ” ሲል አስታውቋል ።

ካሲያስ በ39 አመቱ ጓንቱን የሰቀለ ሲሆን ከሪያል ማድሪድ በ2015/16 ፖርቶን ተቀላቅሎ ነበር በትናንትናው እለት እግር ኳስ በቃኝ ያለው ካሲያስ በአጠቃላይ 881 ጨዋታዎችን ተጫውቶ 31 ቢጫ ካርድ እና 2 ቀይ ካርድ ተመልክቷል ።

ይህ ድንቅ ግብ ጠባቂ
🏆2 የአውሮፓ ዋንጫ (ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር)
🏆1 የአለም ዋንጫ (ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር)
🏆3 ሻምፒዮንስ ሊግ ( ከሪያል ማድሪድ ጋር )
🏆5 የላሊጋ ሻምፒዮን ( ከሪያል ማድሪድ ጋር )
🏆2 የስፓኒሽ ካፕ ( ከሪያል ማድሪድ ጋር )
🏆4 የስፓኒሽ ሱፐር ካፕ ( ከሪያል ማድሪድ ጋር )
🏆1 የፖርቹጊዝ ሻምፒዮን (ከ ፖርቶ ጋር )
🏆1 የፊፋ የአለም የክለቦች ዋንጫ ( ከሪያል ማድሪድ ጋር )
እና በርካታ ድሎችን ማሳካት ችሏል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.