የዝውውር ዜናዎች

ሊቨርፑሎች በባየርሙኒኩ ስፔናዊ አማካይ ቲያጎ አልካንትራ ዝዉዉር ከፒኤስጂ በተሻለ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን Mundo Deportivo ዘግቧል፡፡

የቫሌንሺያው ተጫዋች ፌራን ቶሬስ ዛሬ የማንችስተር ሲቲን ዝወውር እንደሚያጠናቅቅ እና ለዝውውሩም 37 ሚ ፖ እንደሚወጣበት ተዘግቧል፡፡

ቼልሲ ለባየር ሌቨርኩሰን ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ የነበረውን ካይ ሃቬርዝን ለማዘዋወር 45 ሚ ፓ እና ብቃቱ እየተታየ የሚጨመር 9 ሚ ፓ ማቅረባቸው እየተነሳ ሲሆን የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ለዚህ ተጫዋች እስከ 80 ሚ ፓ ለማውጣት መዘጋጀታቸውን Evening Standard ዘግቧል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ እና ቦሩሲያ ዶርትመንድ በጄደን ሳንቾ ዙሪያ እንደተስማሙና በዚህ ሳምንትም በ5 አመት ኮንትራት በይፋ ማንችስተርን ሊቀላቀል እንደሚችል BBC Sport ዘግቧል።

ብራዚላዊዉ የክንፍ አጥቂ ዊሊያም በቼልሲ የቀረበለትን የ2 አመት ውል አለመቀበሉን ተከትሎ በ175,000 ሳምንታዊ ደሞዝና በ3 አመት ኮንትራት ለአርሰናል ለመፈረም እየተስማማ እንደሆነ BBC Sport ዘግቧል፡፡

ኢንተር ሚላን በአሌክሲስ ሳንቼዝ የቋሚ ዝውውር ዙርያ ከማንችስተር የናይትድ ጋር መስማማታቸው እየተነሳ ይገኛል፡፡

ኮሮና ባስከተለው የፋይናስ ቀውስ ምክንያት ባርሴሎና ኔይማርን የማስፈረም እቅድ እንደሌለው የክለቡ ፕሬዝዳንት አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.