ናፖሊዎች ናይጄሪዊውን የሊል አጥቂ ቪክቶር ጀምስ ኦሲማንን የግላቸው ማድረግ ችለዋል ፡፡

በቀድሞ የኤሲሚላን አለቃ በጄራኖ ጋቱሶ የሚመሩት ናፖሊዎች ናይጄሪዊውን የሊል አጥቂ ቪክቶር ጀምስ ኦሲማንን የግላቸው ማድረግ ችለዋል ፡፡
ናፖሊዎች የአጥቂ መስመራቸውን ይበልጡኑ ለማጠናከር ነው ቪክቶር ኦሲማንን በ50 ሚሊዮን ዮሮ ነው ወደ ሳን ፓውሎ ያደረሱት ፡፡

በዘንድሮ አመት ናፖሊዎች የአውሮፓ መድረክ ለማግኘት እጅግ የተቸገሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዐት ሴሪያው 7 ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።
ናፖሊዎች ጁቬንቱስን በመረታት የኮፓ ኢታሊ ሻምፒዮን መሆናቸው ይታወሳል ፡፡

ኦሲማን በናፖሊ ቤት እስከ 2025 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት የፈረመ ሲሆን በፈረንሳይ ሊግ ዋን የነበረውን ድንቅ አቋም በ ጣሊያን ሲሪያ እንደሚደግመው ይገመታል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.