ማንችስተር ዩናይትድ ከሞናኮ ጋር በቤኖይት ባዲሺሌ ጉዳይ እየተደራደሩ ነው ::

ማንችስተር ዩናይትድ ከሞናኮ ጋር በቤኖይት ባዲሺሌ ጉዳይ እየተደራደሩ ነው ተብሎአል።ይሄን የ19 አመት የመሀል ተከላካይ ሪያል ማድሪድም ራፋኤል ቫራንን ለመተካት ይፈልገዋል።

ለቀጣዩ አመት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ማለፉን ያረጋገጠው ሊድስ ዩናይትድ። ኤሚ ቡዌንዳን ከወረደው ኖርዊች ማስፈተም ይፈልጋሉ።20 ሚልዮን ፓውንድም ያስወጣቸዋል።

የባርሴሎናው አለቃ ጆሴ ባርቶሚዮ በአሁኑ ሰአት ኔይማርንም ሆነ ላውታሮ ማርቲኔዝን ምናስፈርምበት ባጀት የለንም አሉ።

ጁቬንቱስ የሮማውን ተስፈኛ ወጣት ኒኮሎ ዛኒዮላ በዚህ ክረምት ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ነው።

ሚካኤል አርቴታ ከባርሴሎናው ኢቫን ራኪቲች ጋር ድርድር ጀምሯል ሲል Le10sport ዘግቧል። የቀድሞ ክለቡም ሴቪያ ማረፊያው ሊሆን ይችላል።

ሪያል ማድሪድ አጥቂውን ቦርጃ ማዮራል ለላዚኦ በ20ሚልዮን ዩሮ ሊሸጥ ስምምነት ላይ ደርሷል ሲል Marca ዘግቧል።

የቶቴንሃሙ ጂያን ቬርቶንገን ከሮማ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። በነፃ ዝውውርም ይቀላቀላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.