ማንቸስተር ዩናይትድ ከ 40,000 ደጋፊዎቹ በታደሙበት በኦልትራፎርድ ይጫወታል
ማንቸስተር ዩናይትድ ከ 40,000 ደጋፊዎቹ በታደሙበት በኦልትራፎርድ ይጫወታል
ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የክለቡን 40,000 ያህል ደጋፊዎች ምስሎችን እና የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ፅሁፎችን በሞዛይክ ባነር ላይ በኦልትራፎርድ እንደሚያስመለክት አሳውቋል፡፡
ክለቡ ከቀናት በፊት ደጋፊዎቹን ፎቶዋቸውን በይፋዊ የክለቡ ገፅ ላይ እንዲጭኑ ጠይቆ የነበረ ሲሆን በጨዋታ ቀንም ደጋፊዎቹ እንዳይሰባሰቡ በማሰብ ሁሉም የክለቡን ቁሳቁስ መሸጫ ሱቆች እንደሚዘጋ አስታውቋል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ ከቶትንሀም ጋር አርብ ምሽት ከሚያደርገው የሜዳው ውጪ ጨዋታ በኋላ ከኮቪድ 19 ወረርሺኝ መልስ የመጀመሪያው የሜዳው ጨዋታውን ከሼፍልድ ዩናይትድ ጋር በቀጣዩ ረቡዕ ያደርጋል፡፡