የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 32 ጨዋታዎችና የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ፕሮግራም ይፋ ሆነ!

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በመጪው ሰኔ 10 እንደሚጀመር ይታወቃል ታድያ ይህንንም ተከትሎ አወዳዳሪ አካሉ ከሰኔ 10 ጀምሮ የሚካሄዱ 32 ጨዋታዎች መች እና በስንት ሰዐት እንደሚካሄዱ ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት ሊጉ  እሮብ ሰኔ 10 አስቶንቪላ ከ ሼፊልድ ዩናይትድ በሚያረጉት ጨዋታ ተጀምሮ ሃሙስ ሰኔ 25 ማንችስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል እስከሚያደርጉት ጨዋታ ድረስ ያሉት ፕሮግራሞች ይፋ ተደርገዋል።

ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተጨማሪ የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎችም ፕሮግራም ይፋ የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት፥

ቅዳሜ ሰኔ 20: ኖርዊች ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ 11:30

እሁድ ሰኔ 21:  ሼፍልድ ዩናይትድ ከ አርሴናል 7:00

ሌስተር ሲቲ ከ ቼልሲ 10:00

ኒውካስትል ከ ማንችስተር ሲቲ 12:30 ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይፋ ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.