ጆርጅ ፍሎይድ በስፖርቱ

May 25 2020 ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በአሜሪካ ግዛት በሆነችው ሚኒፖልስ በግዛቱ ፖሊስ ደርክ ቻውቪን 8 ደቂቃ ሙሉ አንገቱ ላይ ተረግጦት ትንፋሽ አጠረኝ እያለው ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ይህም ድርጊት በመላው አሜሪካ እና በአለም ተቃውሞ እና ውግዘት አስከትሏል። ይህንንም ድርጊት በስፖርቱ አለም ያሉ ሰዎችም ከማይክል ጆርዳን እስከ ፖል ፖግባ ከኮሊን ካይፐርኒክ እስከ ሴሪና ዊሊያምስ ከታይገር ዉድስ እስከ ሊዊስ ሃሚልተን ከዴቪድ ቤካም እስከ ጃደን ሳንቾ ከታኮሚ ኦሳካ እስከ ክሪኬት ተጫዋቹ ዳረን ሳሚ ከማጂክ ጆንሰን እስከ ማርከስ ቱራም ሁሉም በአንድ ድምፅ ተቃውመውታል።

 

በቡንደስ ሊጋው ጃደን ሳንቾ በሳምንቱ መጨረሻ ዶርትሙንድ ከፓደርቦርን ባደረጉት ጨዋታ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ቲሸርቱን በመግለጥ “ፍትህ ለጆርጅ ፍሎይድ” የሚል ፅሁፍ አስነብቧል በዚህ ጨዋታ ሃጅራፍ ሃኪሚ ተመሳሳይ ፅሁፍ አሳይቷል። የቦሪሲያ ሞንቼ ግላድባ ተጫዋች ማርከስ ቱራም በመንበርከክ ተቃውሞውን ገልፁል።ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ከማይክል ጆርዳን በድርጊቱ በጣም እንዳዘነ እና በሰላማዊ መንገድ ድምፃችንን ማሰማት አለብን በማለት መልክቱን አስተላልፏል።የምንጊዜም የማንቸስተር ዩናይትድ እና ማድሪድ ኮኮብ ዴቪድ ቤካም፣ ፖል ፖግባ እንዲሁም ማርከስ ራሽፎርድ ድርጊቱን ተቃውመውታል። እንዲሁም ሊቨርፑል እና ቼልሲዎች በልምምድ ወቅት በመንበርከክ ድርጊቱን አውግዘዋል። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማጂክ ጆንሰን እስከመቼ ነው ጥቁሮች መንገድ ላይ እየተገደሉ ምናየው በማለት ነገሩን በምሬት አወግዟል። ታዳጊዋ የቴኒስ ተጫዋች ኮኮ ጋፍ ቀጣይስ ማን ነው እኔ ነኝ በማለት ከስፖርተኞች ጠንከር ያለ መልዕክት በቪዲዮ አስተላልፋለች። ሁሉም ግን አንድ ነገር ይላሉ “የጥቁሮች ህይወት ትርጉም አለው”።

Leave a Reply

Your email address will not be published.