ሳውዝምፕተን 0 – 9 ሌስተር ሲቲ

•በዛሬው ጨዋታ ሌስተር ሲቲ ያገባው የጎል ብዛት በዘንድሮ የውድድር ዘመን እስከአሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ፣ ሼፍልድ ዩናይትድ፣ ኤቨርተን እና ኒውካስትል ዩናይትድ ካገቡት ጎል በሙሉ የሚበልጥ ሲሆን ከብራይተን እና ሳውዝምፕተን ጋር እኩል ነው
•ሌስተር ሲቲ በ 131 ዓመታት የእንግሊዝ ከፍተኛ ሊግ ታሪክ ውስጥ ከሜዳ ውጪ ብዙ ያገባው ክለብ ሆኗል
•ሌስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ የተመዘገበውን በብዙ ጎል የማሸነፍ ሪከርድ ተጋርቷል (በ ማርች 1995 እ.ኤ.አ ማን.ዩናይትድ 9 – 0 ኢፕስዊች ፣ ኖቬምበር 1995 እ.ኤ.አ ቶትነሀም 9 – 1 ዊጋን)
•አዮዜ ፔሬዝ በአንድ ቡድን ላይ ሁለት ጊዜ ሀትሪክ በመስራት ሉዊስ ሱዋሬዝ ኖርዊች ሲቲ ላይ ያደረገውን ታሪክ ተጋርቷል
•ሳውዝሃምፕተን በሊግ ታሪካቸው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳቸው 9 ግቦችን አስተናግደዋል
•የሌስተር ሲቲዎቹ (ፒሬዝ እና ቫርዲ) በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ውስጥ ሁለት ተጨዋቾች በተመሳሳይ ጨዋታ ለየብቻቸው ሶስት ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ በመስራት ሁለተኛው የአንድ ቡድን ተጫዋቾች ያደርጋቸዋል (በሜይ 2003 እንዲሁ የአርሰናሎቹ ፔናንት እና ፒሬዝ ከሳውዝሃምተንተን ጋር በተመሳሳይ ሀትሪክ ሰርተው ነበር)
•ሌስተር ሲቲ ዋንጫ ባነሳበት 2015/16የውድድር ዘመን በ10ጨዋታ ካገኘው 19 ነጥብ የአሁኑ የውድድር ዘመን በአንድ ይበልጣል( በ10ጨዋታ 20 ነጥብ)
•ሌስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በመጀመሪያ አጋማሽ ላይ አምስት ግብ ያስቆጠረ ሁለተኛው ቡድን ያደርገዋል (የመጀመሪያ ማንቸስተር ሲቲ ባለፈው ኤፕሪል በርንሌ ላይ ያስቆጠረው አምስት ጎል ነበር)

Leave a Reply

Your email address will not be published.