የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

ለ14ተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ዋንጫ በቀጣዩ ቅዳሜ ጥቅምት 22 እንደሚጀመር ታውቋል፡፡ በውድድሩም ኢትየጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መከላከያና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከከተማው ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን ሰበታ፣ ወልቂጤ፣ ወልዋሎ እና ባህርዳር ከተማ በተጋባዥነት ይሳተፋሉ፡፡
ይህን በማስመልከት የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ዛሬ ጠዋት በማዘጋጃ ቤት የተካሄደ ሲሆን በዚህም፤

ምድብ 1
? ቅ/ጊዮርጊስ
? ባህር ዳር ከተማ
? ወልቂጤ ከተማ
? መከላከያ

ምድብ 2
? ኢትዮጵያ ቡና
? ኢትዮ-ኤሌክትሪክ
? ወልዋሎ አ.ዩ.
? ሰበታ ከተማ

ውድድሩ ቅዳሜ ጥቅምት 22 ሲጀመር
⚽️ ባህር ዳር ከ ወልቂጤ …….. 8፡00 ሰዓት
⚽️ ቅ/ጊዮርጊስ ከ መከላከያ …….. 10፡00 ሰዓት

እንዲሁም ሰኞ ጥቅምት 24
⚽️ ኤሌክትሪክ ከ ወልዋሎ …….. 8፡00 ሰዓት
⚽️ ኢትዮጵያቡና ከ ሰበታ …….. 10፡00 ሰዓት
በመጀመሪያ ጨዋታ የሚገናኙ ሲሆን ውድድሩም የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚያገኝ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.