“ይህ ለሊቨርፑል ነው”

አንድሪው ሮበርትሰን ( ግንቦት 29 2019 እ.ኤ.አ.)
(ክፍል 1)

በመናዘዝ መጀመር እፈልጋለሁ ፡፡ ብዙ ነገሮች አያሳስቡኝም ፣አንድ የሚያሳስበኝ ነገር ካለ ግን የእግር ኳስ ታሪኬ ተረት ነው የሚል ሀሳብ ነው ፡፡
ሰዎች ተወዳጅና ተፈላጊ ሰው ስለመሆኔ ሲያወሩ ለማደነቀና ለማሞገስ ብለው እንደሆነ አውቃለሁ፤ ይህንንም አደንቃለሁ፣ ነገር ግን የልብ ስሜቴን ስናግር ፤ እውነት ስላልሆነ እንደ ትክክለኛ አስተያየት አልቆጥረውም፡፡

በዙሪያዬ ምንም የአስማት ነገር አልተንቀሳቀሰም ፣ በዓለም ካሉት ታላላቅ ክለቦች በአንዱ ላይ ለመጫወት አንድ ዓይነት የሎተሪ ዕጣም አላሸነፍኩም ፡፡ የሊቨርፑል ተጫዋች የሆንኩበት ምክንያት የአገሬ አምበል ካደረገኝ ምክንያት ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ያለሁበትን ቦታ ለመድረስ በመንገዴ ላይ የቆሙትን መሰናክሎች ለማስወገድ ሰርቼያለሁ ፣ እናም ያንን በማድረግ ያለኝን ተሰጥኦ ውጤታማ ማድረግ ችያለሁ ፡፡

ይህ መተረኬ/ማድረጌ ለምን አስፈለገ? በእውነቱ እንደ ግለሰብ ለእኔ ብዙ ግድ አይሰጠኝም ፡፡ ምናልባት ለቤተሰቦቼም ግድ ላይሰጣቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ያስፈልጋል ምክንያቱም አምላክ ምን ያህል አንዲ ሮበርትስቶች በዚህ ምድር እንደሚገኙ ያውቃል። ሰዎችን ለማሳመን እየታገሉ ያሉ ልጆች ለችሎታቸው እድል ይገባቸዋል ። ልጆች መሆን ወደሚገባቸው ቦታ ለመድረስ ሰብረው የሚገቡበት አጋጣሚ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ተስፋ ቆርጠው እጅ ለሚሰጡ ልጆች ይህን ከማድረግ የሚቆማቸው እውነተኛ የሆነ ተረት ብቻ ነው፡፡
የጋዜጦች የፊት ለፊት ገጽ ማድመቂያ መሆን በጭራሽ አልፈልግም ፣ ነገር ግን በማንኛውም አጋጣሚ የምሆን ከሆነ ፣ ይህ መሆን አለበት – ተስፋ ካልቆረጣችሁ እና ሌሎች በሚጠራጠሩበት ጊዜ በራሳችሁ ማመን ከቀጠናችሁ እናንተም ማድረግ ትችላላችሁ። ምን ያህል ጥሩ እንደሆናችሁ ማሳየት ትችላላችሁ።
አሁን ሁለት የራሴ ልጆች አግኝቻለሁ ፣ ይህ መልእክት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው ፡፡ አባታቸው ጥሩ እድል አግኝቷል ብለው እንዲያስቡ አልፈልግም ፡፡ ያላቸውን አቅም ሁሉ መጠቀም የሚችሉት አዕምሮአቸውን ከተቀበለው ብቻ መሆኑን እንዲገነዘቡ እፈልጋለሁ ፡፡ ተረት? ያ ከመኝታ ሰዓት የሚነገራቸው ነገር ነው።
ስለ እግር ኳስ በጣም ጥሩ ከሆኑት ነገሮች አንዱ እንደ እኔ ያሉ ብዙ ሰዎች መኖራቸው ነው። ብዙ ተጫዋቾች በብዙ ልፋት ከፍተኛውን ደረጃ ይይዛሉ። እኔ ያለሁበት የሊቨርፑል ቡድን እንደዚህ ያሉ ተጫዋቾች እጥረት የለውም።

ለምሳሌ ቨርጂል ቫን ዳይክን ውሰዱ ፤ የዓለማችን ምርጡን የመሀል ተከላካይ። ስንት አሰልጣኞች እና መልማዮች እንደተመለከቱት እና ትልቅ ላይሆን ይችላል ብለው ያስቡ ነበር? ብዙ እንደነበሩ እሱ ራሱ ይነግርዎታል።

ዛሬ ከምርጥ ጎል ጨራሾች መካከል አንዱ የሆነው ሞህ ሳላህ፣ አንድ ጊዜ በከፍተኛ ፕሪሚየር ሊግ ቡድን ጥሩ አደለህም ተብሎ ተጥሎ ነበር ፡፡
ዮርዳን ሄንደርሰን ችሎታውን በመጠራጠር የተጠየቀባቸውን ጊዜያት ብዛት መቀነስ ነበረበት – ምንም እንኳን በበቂ ሁኔታ ከእርሱ ጋር አብሮ ለመሥራት እድለኛ የሆነ ማንኛውም ሰው ባይኖርም – እዚህ ግን ለሁለተኛ ተከታታይ በሻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑልን በአምበልነት እየመራ ለፍፃሜ ለማቅረብ ዝግጁ ሆኗል ፡፡
ወደፊት መቀጠል እችላለሁ ፣ በእውነቱ ማድረግ እችላለሁ ፡፡ እነዚህ ሁሉ ተረት ተረቶች ከሆኑ ፣ ከሃንስ ክርስቲያን አንደርሰን በላይ ተረቶች አለን ማለት ነው ፡፡ እነዚህ አፈ ታሪኮች ብቻ ግን አይደሉም ፤ ቢሆኑም ሁሉም ልዩ የሚያደጋቸው የትጋት እና ቁርጠኝነት ምሳሌዎች ናቸው።

ይህ ለእኛ እንደ አንድ ቡድን እንደሊቨርፑልም እንደ ክበብም ለእኛም ይሠራል ፡፡ እኛ እንደ ቡድን እዚህ ጋር የሆንበት ወይም የቆምንበት ምክንያት በሥራ ቦታ ስነ-ምግባራችን እና ሁሉም ነገር ይቻላል የሚል እምነት ስላለን ነው ፡፡ ይህ ምክንያትም እኛ ታላቁን ባርሴሎና ቡድን ላይ ከ 3 ለ 0 መመራት ተነስተን እንድናሸንፍ ረድቶናል፡፡ ዕድል በእጁ እስኪጫወትልን ድረስ አልጠበቅንም እና ተስፋ አድርገን አልጠበቅነውምም ፣ እጣ ፈንታችን በመንገዳችን እንዲሄድ አስገድደናል እንጂ የአለማችንን ምርጡ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲን እንኳን ከፊታችን እያየን ሊያቆመን አይችልም ፡፡

ምናልባት ከሊቨርፑል ውጪ ያሉት ይህንን አድርገን ወደ ፍፃሜ ያልፋሉ ብለው አልጠበቁ ይሆናል፡፡ ለእነሱ በእውነቱን ይህን ለማሰብ ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሏቸው፤ በተለይ በኑዩ ካምፕ የደረሰብን ደንበኛ ሽንፈት፡፡ ስለ መጀመሪያው ጨዋታ የሆነ አንድ እምነት ነበረን ፡፡ ከባርሴሎና ጋር መፎካከር እንድንችል በቂ ዝግጅት አድርገን ነበር፡፡ ችግሩ የጨዋታው ወሳኝ አጋጣሚዎች በሙሉ ከኛ በተቃራኒ የቆሙ መሆን ነበር፤ ሆኖም ከኋላችን በአንፊልድ ሞገድ ያንን ልንቀለብሰው እንደሚችል እናውቃለን ፡፡
የሩህሩህ የምባል ዓይነት ሰው ብሆን ኖሮ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምሽት ጨዋታዎች ላይ ወደ አንፊልድ ለሚመጡ የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ምናልባት አዝንላቸዋው፡፡ የሚገጥማቸው ነገር ለነሱ ፍትሃዊ አይደለም ማለት ይቻላል። አስገራሚው ታሪክ፣ ጥልቅ የፍቅር ስሜት እና የማይነቃነቅ/የማይናወጥ እምነት እና አመለካከት ለተጋጣሚ ገሃነም ነው ለእኛ ደግሞ በጣም ተጠቃሚ አድርጎናል፣ ለዚህም ነው ሊቨርፑል በብዙ አጋጣሚዎች ተጋጣሚዎቹን ያሸነፈው፣ እናም ለዚህ ነው ደጋፊዎቻችን እምነታቸውን ይዘው የሚመጡት ይህም የማይቻል ነገር የሚቻል ያስመስለዋል ፡፡ ከዚህ በፊት አይተውታል ፣ ስለሆነም ለምን አይጠብቁም;
በመልበሻ ክፍል ውስጥ እያለን እና ወደጨዋታው ልንገባ ስንል ዕድል እንዳለን እናውቅ ነበር፡፡ አሰልጣኛችን በእኛ ላይ እምነት አለው፤ ምክንያቱም ነግሮናል፡፡ እናውቃለን ደጋፊዎቻችን በእኛ ያምናሉ ምክንያቱም መስማት እየቻልን ነው፡፡ አምላኬ! እየሰማናቸው ነው፡፡ እና ምናልባትም ከሁሉም በጣም አስፈላጊ የሆነው እኛ በራሳችን እና በእያንዳንዳችን እንደምናምን አውቀናል ፡፡
ለዚያ ነው ልክ ዲቮክ ኦሪጊ በሰባተኛው ደቂቃ ጎል ሲያስቆጥር፣ ኦ በቃ አላምንም ፡፡ አውቅ ነበር፣ ምን እንደሚመጣ አውቅ ነበር፤ ….

(ይቀጥላል…)

Leave a Reply

Your email address will not be published.